Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, December 20, 2015

የህወሓት የደንነት ቢሮ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን አስጠነቀቀ



የደንነት መስሪያ ቤቱ በሚንስትሮች ምክር ቤት በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያ የሰባት ቀን የጌዜ ገደብ የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ ታውቆአል። የደህንነት መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ ውስጥ ሳይታሰብ የፈነዳውን አመፅ ለመቆጣጠር ምን አይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ሙሉ ስምምነት ላይ መድረስ አልችል ብሎ ሲወዛገብ መሰንበቱ ሲታወቅ ዛሪ ከጥዋት ጁምሮ ሲአካሂድ በዋለው ውይይት ላይ ግን ማንኛውንም አይነት ሀይል ተጠቅሞ አመፁን ለመቆጣጠር ወስኖአል። የውሳኔውን ቅጅ ከ አንድ ሳምንት ማስጠንቀቂያ ጋር በአቶ ካሳ ተክለብርሀን በኩል ለጠቅላይ ሚንስትሩ ልኳል።
የአቶ ሀይለማርያም አስተዳደር አመፁን ለመቆጣጠር መመሪያ ከአሜሪካ መንግስት መቀበሉን በአስቸኳይ አቁሞ የተነሳውን መጠነ ሰፊ አመፅ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መቆጣጠር የሚያስችል የኦፕሪሽን መርሀ ግብር አውጥቶ ለፊደራል ፓሊስና መከላከያ ማስረከብና ለተግባራዊነቱም ካልተንቀሳቀሰ ሙሉ ሰላም የማስከበሩን ስራ መከላከያ ይረከባል ይላል። በአጭሩ መፈንቅለ መንግስት ይደረጋል ማለት እንደሆነ ምንጮቸ አረጋግጠዋለል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials