ወያኔ በሰሜን ጎንደር ችግር እንዳለ አመነ - የሚሊዮኖች ድምጽ
በሰሜን ጎንደር ወደ መተማ የሚወስደው መንገድ እንደተዘጋ በስፋት መዘገቡ ይታወቃል። መረጃዎችን የወያኔ ሜዲያዎች ለመደበቅ ሙከራ ቢያደረጉም፣ በአካባቢው እየተከሰተ ያለው ቀዉስ ግን በስፋት በሶሻል ሜዲያ ሰፊ ዘገባ እያገኝ ነው።
ችግሩ በጣም ከመባባሱ የተነሳ ፣ በሚቆጣጠረው ፋና ራዲዮ በኩል፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በጎንደር አለመረጋጋት እንዳለ አምኗል።
"የክልሉ መንግሥት ከጭልጋ እስከ መተማ ባሉ አካባቢዎች በፀረ-ሰላም ኃይሎች የተፈጠረውን ሁከትና ግርግር ለማስቆም ሰላም ወዳድ ከሆነው የአካባቢው ህበረተሰብ ጋር በቅርበት እየሰራ ነው ብለዋል። " ሲል ነው ፋና የዘገበው።
በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያና በሰሜን ጎንደር አለመረጋጋት እንዳለ ያመነው አግዛዙ፣ በሌሎች ቦታዎች ቀዉስ እንዳይፈጠር ለማድረግ ደፋ ቀና እያለ ነው። አዲስ አበባን ጨመሮ በጎጃም፣ በወሎ ተቃዉሞ ሊነሳ እንደሚችል ይነገራል። ለወያኔዎች ሁኔታዎች በሁሉም አቅጣጫ ከቁጥጥር ዉጭ እንደሆነባቸው ምልክቶች እየታዩ ነው።
No comments:
Post a Comment