Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 1, 2015

አርበኛ ተስፋሁን አለምነህ ከኤርትራ በርሃ



አርበኛ ተስፋሁን አለምነህ ከኤርትራ በርሃ
------------------------------------------

የምስራቅ አፍሪቃ መንግስታት ካላቸዉ አባገነንነት የተነሳ የጎንዮሽ ትብብራቸዉ ስልጣናቸዉን ማስቀጠል ላይ መሰረት ያደረገ ነዉ። የሃገር ሉአላዊነትን ባላስጠበቀ መልኩ መንቀሳቀስ ደግሞ ለወያኔ ልምዱ ነዉ። የኢትዮ-ሱዳን በአዲስ መልክ የድንበር. ማካለል እንደ ሚደረግ የሱዳኑ ትሪቡን ጋዜጣ መዘገቡን ተከትሎ ግጭቱ አገርሽቶ ወደ ለየለት የሞት ሽረት እያመራ ነዉ።


ግጭቱ በወያኔ እና በአልበሽር መሃከል እንዳልሆነ ይታወቃል። ከአሁን በፊት ከፍተኛ የሆነ ደም ፈሶበታል። አሁንም በባሰ ሊፈስበት ነዉ። የአልበሽር መንግስት ወያኔ የቀጠናዉ አወናባጅ እንዲሆን ላበረከተዉ አስተዋጦ ተጨማሪ የእጅ መንሻ በመጠየቅ ላይ ነዉ። የወያኔ ደሕንነቶች ከአዲስ አበባ ይልቅ ካርቱም ላይ እንደ ጉንዳን እየተተረማመሱ ለሚፈነጩበት ዉለታ የኢትዮጵያ ግዛት ለሱዳን ይሰጣሉ። አንድ ሃቅ አለ። ለለዉጥ ሃይሉ የሱዳን ያህል እንቅፋት የሆነ የለም። በመሆኑም አልበሽር እንቅፋት መሆኑን ቢያቆም በቅርብ ጊዜ ወያኔ ምን እንደሚገጥመዉ ጠንቅቆ ያዉቃል። ይህን ስለ ሚፈራ ብቻ በተበርካኪነት ለሱዳን ሁሉን ያደርጋል።

ሌላዉ ስጋቴ ነዉ የሚለዉን አማራን ከሱዳን ጋር እንዳይወሰን ቀድሞ ሰረቷል። የፀረ ኢትዮጵያ አቋሙን ለማስፈጠም።ጎጃም መተከል ማንኩሽ ወደ ቤንሻጉል ከከለለ በሗላ ለሱዳን ሲሰጥ ሲጠየቅ ምን አገባህ በጉምዝ መሬት ጎንደር ሁመራ ለትግሬ ተከልሎ ልጉድ ለሱዳን ሲሰጥ ለምን ምን አገባህ በትግሬ መሬት(ምን አገባህ በትግሬ መሬት የተደገመ ነዉ ) ራሴን የአይን ምስክር አድርጌ ማስቀመጥ እችላለሁ።

ለለዉጥ ሃይሉ አልበሽር እንቅፋት ነዉ። <<ሰጥቶ መቀበል>> ከለዉጥ ሃይሉ አያዋጣም። ቢልም የለዉም። አንድ ነገር ግን እንችላለን። እሱም ኢትዮጵያን በጠበጃ ከሚገዛት ጋር የሚደረግ ስምምነት ተቀባይነት እንደለለዉ አልበሽርም ተጠቃሚ እንደማይሆን ማሳወቅ በተግባር ከህዝቡ ጋር መዋደቅ ከአራት አመት በፊት የነበረዉ አሁን የለም። የሱዳን ድንበር ከሞላ ጎደል አዉቀዋለሁ። ምን እኔ ብቻ ጠቅላላ የለዉጥ ሃይሉ ያዉቀዋል። በግልፅ ለመናገር የአሁኑ መሬት መሰረታዊ የሆነ በኢትዮጵያ ካርታ ላይ ለዉጥ ያመጣል ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ በሙሉ ሱዳናዊ ሆነ ማለት ነዉ። የጆግራፊ ትምህርትም አይጠይቅ ለማወቅ የምንጠብቀዉ ጉዳይም አይሆንም። ለዚህ ድንበር መድረስ ካልቻልን ለምንም አንደርስም። በምንም ተአምር ይህ ጉዳይ አንድ አድርጎ የለዉጥ ሃይሉን ወደ አንድነት ካላመጣን እዉነትም ኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ ቁሟል። በሃገር ዉስጥም በዉጭም ኢትዮጵያዊ የሆነ የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆነ ድምፁን ያሰማ። ሚዲያዎች ለህዝብ አድርሱ።አክቲቨስቶች አቀጣጥሉ።ህዝብ ይነቃነቅ ታጋይ ትጥቅህን አጥብቅ። የወያኔ ፍፃሜ የነፃነነት ጅማሬአችን ይሆናል።




No comments:

Post a Comment

wanted officials