Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, December 3, 2015

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አገራዊ ጸረወያኔ ትግሉን ተቀላቀለ

የጎንደር ዩንቭርስቲ አገራዊ ጸረወያኔ ትግሉን ተቀላቀለ
ይለያል ዘንድሮ የወያኔኖሮ
Patriotic Ginbot 7's photo.


(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

‪#‎በጎንደር‬ ከተማ በሚገኘው የህወሓት ወህኒ ቤት ዛሬም በርካታ እስረኞች በጥይት ተጨፈጨፉ፤ ከተማዋ በጠቅላላ ትግረኛ ተናጋሪዎች ብቻ በሆኑ ወታደሮች ተወራ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፤ ጎንደር ዩኒቨርሲቲም ተረብሿል፡፡
====================================================
በጎንደር ከተማ የሚገኘው የህወሓት ግዙፍ ወህኒ ቤት በእሳት ከነደደ በኋላ ከጥይት እና ከእሳት ቃጠሎ የተረፉት እንዲሁም በተጨማሪ ማምለጥ ያልቻሉት እስረኞች ከከተማው ውጭ በአንገረብ ወንዝ ግድብ አቅራቢያ ወደሚገኝ ሌላ አዲስ ወህኒ ቤት የተዛወሩ ሲሆን እስረኞቹ ቃጠሎው ከተነሳበት ማክሰኞ እለት ጀምሮ ምግብና ውሃ ፈፅሞ አልተሰጣቸውም፡፡
በዛሬው ዕለት የእስረኞች ቤተሰቦች እንዳይጠይቁ በመከልከላቸው ምክንያት በአዲሱ ወህኒ ውስጥ ከፍተኛ አመፅ ተነስቶ ከአስር በላይ እስረኞች ተገድለዋል፤ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል፤ ወህኒውን ሰብረው ያመለጡም እንዳሉም ታውቋል፡፡
የህወሓት አገዛዝ በክልሉ አስተዳደር ላይ ምንም አይነት እምነት በማጣቱ ትግርኛ ተናጋሪዎች ብቻ ያሉበት ጦር ከሁመራና ከሌሎች የትግራይ አካባቢዎች አጓጉዞ ጎንደር ከተማን ወሯታል፡፡ በመሆኑም በጎንደር ከተማ ሊፈነዳ የተቃረበ የህዝባዊ አመፅ ውጥረት ነግሷል፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲም ተበጥብጦ ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ አጥሩ ዙሪያውን በህወሓት ታማኝ ጦር ተከቧል፡፡
የጎንደር ከተማ በየደቂቃው የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ድምፅ የሚደመጥባት ታላቅ ጦር ሜዳ ሆና ትገኛለች፡፡
ወያኔ ሌባ የሚሉ ተማሪዎቹ መፈክር ያሰሙ ሲሆን የፊድራል ቦሊስና የአገዚ ጦር ግቢውን በስፋት እየሰፈረበት ነው። ይህ በንዲ ህእንዳለ ጎንደር አዲሱ ማረሚያ ቤት አንገረብ ግድብ ሚባለው ቦታ ላይ የተወሰዱት እስረኞች በድጋሚ በስርቤቱ ላይ የሳት ቃጠሉ በመነሳቱ በርካታ ይህሊና እስረኞች ማምለጣቸውን የወያኔ ወንበርጠባቂ የፊድራል ቦሊስና አጋዚ ጦር ዛሬም ከሳት የሚያመልጡትን ይህሊና እስረኞች እንደገደሉ አካባቢው ላይ ያሉ ሰዎች ይናገራሉ 
ፒያሳ ማንም ነዋሪ አይንቀሳቀስም። ዩኒፎርም የለበሱ ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ የልዩ ጦር አባላት ብቻ ይታያሉ
18 መስጊድ የሚባለው ኮሌጂ አካባቢ እስረኞችን ፍለጋ በሚል ቤት ለቤት ፍተሻ የሚደረግ ሲሆን ፣ህዝቡን የማንገላታት እና ፣በቤት ውስጥ የተገኜን ውድ ንብረት ከየት አመጣኽው በሚል የመቀማት ስራ እየተፈፀመበት ነው።
ህዝቡትናንት የተገደሉሸትን ሳይቀብር ዛሬም ሌላ ሀዝን ውስጥ ነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials