የአሜሪካው እጩ ፕ/ት ትራምፕ "ሙስሊሞች ወደ አሜሪካ እንዳይመጡ" ማለታቸው ታላቅ ቁጣ ቀሰቀሰ
“እውነተኛ ሙስሊሞች አሸባሪነትን ጠንቅቀው ያውቃሉ፣በጽኑም የቃወማሉ”አንጋፋው ቡጢኛ መሃመድ አሊ
እንደ ብዙዎች እምነት አሜሪካ የሁሉም የሰው ልጆች አገር ነች ተብሎ ይታመናል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ዘመን አመጣሽ የአሜሪካ ፖለቲከኞች በተወሰኑ የማህበርሰብ ክፍሎች እና የእምነት ተከታዮች ላይ ከረር ያለ ሂስ እና ጥላቻ ሲያሰሙ የሰተዋላሉ። ከእነዚህ ጸረ ባእዳን እና ጸር እንግዳ አመለካከት ካላቸው የአሜሪካ ፖለቲከኞች መካከል ቱጃሩ እና የሪፐብሊካዊያን ፕ/ታዊ እጩ ተወዳዳሪው ዶናልድ ትራምፕ አንዱ ሲሆኑ እርሳቸውም ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ አረፋፈዱ ላይ በአሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት ሰምበርላንዲኖ ክፈለ ከተማ ወስጥ ሁለት ባል እና ሚስት ሙስሊም እክራሪዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ባደረሱት ጥቃት አንድ ኢትዮጵያዊ/ኤርትራዊ ወገናችንን( የ 60 አመቱ አቶ ይሳቅ አምኒዮስን) ጨምሮ 14 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ 20 በላይ መቁሰላቸውን ተከትሎ ባሳልፈነው ሰኞ እለት ትራምፕ በሰጡት አስተያየት “የአሜሪካ ዘግነት ካለቸው በቀር ሁሉም ሙስሊሞች ወደ አሜሪካ ምድር ዝር እንዳይሉ(አንዳይገቡ)”የሚል አሰተያየት በመሰንዘራቸው በርካታ አለማቀፋዊ ተቃውሞ እየተሰንዘረባቸው ይገኛል።
የፕ/ት ባራክ ኦባማ ጽ/ቤትን ጨምሮ ከሁለቱም አወራ የአገሪቱ ፓርቲዎች ( ሪፓብሊካን እና ዲሞክራቶች ) በ ትራምፕ ላይ የከረረ ትችቶች የተሰነዘሩ ሲሆነ አንዳንድ ወገኖች ትራምፕ በዚህ እና መሰል አሰተያየታቸው ሳቢያ ከፕሬዜዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪነት ይወገዱ የሚል ሃሳብ ያቀረቡባቸው ሲሆን ቱጃሩ እና በእሰካሁኑ የሪፐብሊካኖች የሕዝብ አሰተያየት መሪነቱን የያዙት ትራምፕ ግን “ከጀመርኩት የምረጡን ዘመቻ አንዳች ሃይል አያግደንም ካለሆነ የግል ተወዳዳሪ አሆናለሁ “ሲሉ ተደምጠዋል። ቁጥራቸው ከ 300 ሺህ በላይ የእንግሊዝ ዜጎች ትራምፕ በቅርቡ ወደ እንግሊዝ የሚያደርጉት ጉዞ እንዲሰረዝ (አንዳይገቡ)ፊርማ ያሰባሰቡ ሲሆን የእንግሊዙ ቻንሰለር ጆርጅ አዝቦ ግን “ፈሬ ከርሰኪ የሆነ ሰውን ከማግለል በዲሞክራሲያዊ መንገድ አመለካከቱ የተሳሳተ መሆኑን ማሰተማር ይሻላል”በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።
በትራምፕ አሰተያየት ዙሪያ የፊታችን ታህሳስ 28 2015 እየሩሳሌም ውስጥ ትራምፕን የሚያነጋግሩት ከእስራኢሉ ጠ/ሚር ቢኒያም ናትኒያሁ አንሰቶ በርካታ ቱባ ባለሰልጣናት ከመቅጽበት በጽኑ የውግዘት ድምጻቸውን አሰምተዋል ። የእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር ዲቪድ ካሚሮን የትራምፕን ሰሞነኛ አሰተያየትን “ከፋፋይ እና ፋይዳ ቢስ አመለካከት” በለውታል። በ2010 አኤአ የክብር ዶክትሪት ማእርግ የሰጣቸው የሰኮትላንድ ዩኒቨርስቲ በበኩሉ ትራምፕን ማሞገስ ተገቢ ባለመሆኑ ይህንኑ ማርጉን መሰረዙን በ ፌስ ቡክ አማካኝነት ይፋ አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ጠንካራ አሰተያየታቸውን ከሰነዘሩት ታዋቂ የአለማችን ሰዎች መካከል ጥቁሩ አሜሪካዊው እና አንጋፋው የከባድ ቡጢ ሻምፒዮናው መሃመድ አሊ አንዱ ነው። መሃመድ አሊ ትራምፕን በተመለክተ እሮብ እለት በጻፈው መልእክቱ “እኔ ሙስሊም ስሆን ሙስሊም መሆን እና ሰላማዊ ሰዎችን በፓሪስ(ፈረንሳይ)፣ በሰምበርላንዲኖ(አሜሪካ)ወይም በየትኛውም ስፍራ ይሁን መግደል ፍጹም ግንኙነት የላቸውም ።እውነተኛ ሙስሊሞች እራሳቸውን እስላሚክ ጀሃዲስት እያሉ የሚጠሩ አሸባሪዎችን ጥፋት እና አላማ ከሃይማኖታችን ጋር የሚጻረረ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉ።” በማለት የትራምፕን ሰሞነኛ አሰተያየትን ቡጢኛው አሊ አጣሎታል ። ሙስሊሞችም በጋራ በመሆን በእምንት ሽፋን ሽብር እና ሁከት የሚያካሄዱ ወገኖችን እንዲፋልሙ መሃመድ አሊ ጥሪውን አቅርቧል።እጩ ፕ/ታዊው ትራምፕ ግን እሮብ እለት በሰጡት ምላሽ “የአሜሪካ ዜግነት የሌላቸው ሙስሊሞች ወደ አሜሪካ አይገቡ ማለት ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ለጸጥታችን እና ለደህነነታቸን ሲባል ነው።” በማለት በቀደሞው አቋማቸው ጸንተዋል። ይህ በአንዲህ እንዳለ አርብ አረፋፈዱ ላይ በካሊፎርኔያ ግዛት ኮቼሊያ በተባለ ስፍራ በሚገኝ በአንድ የሙስሊሞች መሰጊድ ላይ የተወረወረ የተቀጣጣይ ቦምብ በሕንጻ አምልኮቱ ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን የጥቃቱም መንሴኤ ከሰሞኑ የ እጩ ተመራጩ የ ትራምፕ ጸረ ሙስሊሞች አሰተያየት ጋር የተዛመደ መሆኑን በረካታ የእምነቱ ተከታዮች ሰጋታቸውን እና መሪር አሰተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
ከሰሞኑ ጸረ ሙሰሊሞች አሰተያየታቸው ጋር በተያያዘ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ከፈተኛ ቸረቻሪዎች ከሆኑት የንግድ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው ላንድ ማርክ ግሩፕ (landmark Group ) የተባለው የቤት ማስዋቢያ እና ከትራማፕጋር ቁርኝት ያለው ድርጅት በ ተባበሩት አረብ አሚሪት፣ኩዊት፣ ኳታር እና ሰወዲ አረቢያ የሚያሰራጨቻችው ሸቀጦችን ላልተወሰነ ጊዜያት አቋርጣል።
No comments:
Post a Comment