በጎንደርና በምእራብ ትግራይ ዉጥረት ነግሷል
ቢቢኤን ሬድዮ፦ አዲስ አበባ (ታህሳስ 05/2008)
ቢቢኤን ሬድዮ፦ አዲስ አበባ (ታህሳስ 05/2008)
በቋራ፣በመተማና በሸንፋ በአካባቢዉ ታጣቂ አማጺያንና በመንግስት ታጣቂዎች መካከል ሳምንቱን ሙሉ የተኩስ ልዉዉጥ አለመቋረጡን፣ የሞቱ ሰዎች መኞራቸዉ፣መንገድ መዘጋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢኤን ገልጸዋል።
በምእራብ ትግራይ ወልቃይት ጠገዴን ወደ አማራዉ መስተዳድር ለመመለስ የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ይህንንኑ በመስጋት ብአዴን የወልቃይት ህዝብንና ኢህአዴግን ለማሸማገል የሚያደርገዉ ጥረት ተቀባይነት እንዳላገኘ ታዉቋል። የወልቃይት ተወላጆች ለቢቢኤን እንደገለጹት ሽምግልና ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የህዝብ ብሶትን ለማለዘብ የሚጠቀምበት የጥቃት መሳሪያ ነዉ። በህወሃት ከላይ ወደ ታች የመጣ መመሪያ ሲቀለበስ ታይቶ የማይታወቅ በመሆኑ ስርዓቱን ቀልብሶ ለዉጥ ከማምጣት በስተቀር አማራጭ የለም ይላሉ።
በብአዴን አስተባባሪነት ከወልቃኢት ወደ አዲስ አበባባና መቀሌ ለኣአቤቱታ የሚንቀሳቀሱ አሸማጋዮች መኖራቸዉን የሚገልጹት የወልቃይት ነዋሪዎች በህወሃት የሽምግልና ማታለያ ዉስጥ ተሳታፊ መሆኑ ‘እኔ ለወልቃይት ህዝብ ማንነት እቆረቆራለሁ፣ ለወልቃይት ህዝብ እታገላለሁ እሰሩኝ፣ ደብድቡኝ ካልያም ግደሉኝ’ ብሎ እራስን አሳልፎ ከመስጠት ተለይቶ የማይታይ በመሆኑ ፋይዳ ቢስ ነዉ ሲሉም የሽምግልናዉን ሒደት ያጣጥላሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም፤በዳንሻ አካባቢ ከሳምንት በፊት ታጣቂ የመንግስት አካላት በአካባቢዉ ካሉ አማጺያንና ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲዋጉ የተሰጣቸዉን ትእዛዝ አንቀበልም ማለታቸዉ ታዉቋል። ከአካባቢዉ ምንጮች ለመረዳት እንደተቻለዉ በመግስት አበል (payroll) ዉስጥ ያሉት ታጣቂዎች “መንግስት ይመጣል፤ መንግስት ይሔዳል። እኛ ግን ከወንድሞቻችን ጋር አብረን መኖራችን ይቀጥላል። ደም የመቃባት ፍላጎት የለንም። መንግስት ከፈለገ ጦሩን አስፍሮ እራሱ ሊዋጋ ይገባል። መሳሪያችንን እንድናስረክብ ከተጠየቅን መሳሪያችንን እናስረክባለን!” ማለታቸዉ ታዉቋል።
አብሮ ለዘመናት በአንድነት የኖረዉን የቅማንት ህዝብን ጎንደር ካለዉ ወገኑ ጋር ለማጣላት ህወሃት መሳሪያ ከትግራይ ወደ ቅማንት እያስገባ መሆኑንን የሚገልጹት ያካባቢዉ ምንጮች፤ ህዝቡ የርስ በርስ ግጭትን እምቢኝ ብሎ አንድነቱን እያጠናከረ መሆኑን ያስረዳሉ።
በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የኢትዮጵያ መሬት እየተቆረሰ ለሱዳን መሰጠቱ፤ ትግራይን ለመለጠጥና ‘ታላቋን ትግራይ’ ለመመስረት መሬት ከአጎራባች ቦታዎች በሙሉ እየተቀነሰ ትግራይን የማስፋፋቱ ሴራ ችላ መባል የሌለበት ነገር መሆኑን የሚገልጹት የወልቃይት ነዋሪዎች፤ ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የተዋከበበትን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ህዝባዊ አብዮትን አምጥቶ ስርዓቱን መቀየሩ ብቸናዉ አማራጭ መሆኑን ይገልጻሉ።
በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የኢትዮጵያ መሬት እየተቆረሰ ለሱዳን መሰጠቱ፤ ትግራይን ለመለጠጥና ‘ታላቋን ትግራይ’ ለመመስረት መሬት ከአጎራባች ቦታዎች በሙሉ እየተቀነሰ ትግራይን የማስፋፋቱ ሴራ ችላ መባል የሌለበት ነገር መሆኑን የሚገልጹት የወልቃይት ነዋሪዎች፤ ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የተዋከበበትን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ህዝባዊ አብዮትን አምጥቶ ስርዓቱን መቀየሩ ብቸናዉ አማራጭ መሆኑን ይገልጻሉ።
“እኛ ህወሃትን አሳምረን እናዉቃለን” የሚሉት ወልቃኢቶች ሰላማዊ ሰልፍና ሽምግልና እድሜዉን የሚያራዝምባቸዉ ዘዴዎቹ ናቸዉ ሲሉ ይገልጻሉ። የሱዳን የመሬት ስጦታ ዉል ከመጠናቀቁና ‘ታላቋ ትግራይ’ ከመመስረቷ በፊት ኢትዮጵያዉያን ሁነኛ ለዉጥን ለማምጣት ሊነሱ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል።
ቢቢኤን መረጃዉን በድምጽ የተቀበለ ቢሆንም፤ ለምጮቹ ደህንነት ሲል የድምጹን መረጃ አየር ላይ ከማዉጣት ታቅቧል።
No comments:
Post a Comment