ፌደራል ፖሊስ የሳተላይት ዲሽን ማዉረድ ጀመረ
ፌደራል ፖሊስ የሳተላይት ዲሽን ማዉረድ ጀመረ
ቢቢኤን አዲስ አበባ ፦(ታህሳስ 08/2008 )
መብራት በማጥፋት የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያን ለመዝጋት የሚሞክረዉ የኢትዮጵያ መንግስት የፌስ ቡክ የመረጃ ፍስትን ለማመናመን ኔትዎርክን ይዘጋል ሲሉ ኢትዮጵያ ያሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ይከሳሉ። ኢትዮጵያ ሚዲያን አፋኝ ተብላ በተለያዩ የስብዓዊ መብት ድርጅቶች ተደጋጋሚ ክስ የሚቀርብባት አገር መሆኗ ይታወቃል።
የቢቢኤን የሱልልታ ምንጮች ዛሬ እንደገለጹን በአካባቢዉ ላይ የተሰማሩት የፌደራል ፖሊሶች የግለሰብ ንብረት የሆኑን የሳተላይት ዲሾች እየነቀሉ መዉሰድ መጀመራቸዉን አሳዉቀዋል። ከዉጪ የሚተላለፉ ሚዲያዎችን እየተከታተላቹ ትረብሻላቹ በማለት የሳተላይት ዲሾችን መዉሰድ የጀመሩት የፌደራል ፖሊሶች ያለምንም ማዘዣ የግለሰብ ንብረትን መዝረፍ መጀመራቸዉ ነው የታወቀዉ። ፈዴራል ፖሊሶች ዛሬ ነቅለዉ መዉሰድ የጅመሩትን የሳተላይት ዲሽ ለግላቸዉ ያርጉት ወይም ወደ መንግስት መጋዘን ለማጠራቀም ይዉሰዱት የሚታወቅ ነገር የለም።
ዛሬ በሱልልታ አካባቢ የፌዴራል ፖሊሶች የሳተላይት ዲሾችን እየነቀሉ መዉሰዳቸዉን የገለጹት የሱልልታ ነዋሪዎች መንግስት እየተፋፋመ ያለዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት ለማስቆምና የመረጃ ፍሰትን ለማመናንመን ምን አልባት ተመሳሳይ የሳተላይት ዲሽ ዘረፋ በተለያየ የኢትዮጵያ ክልል ሊፈጽም ይችላል ሲሉ ስጋታቸዉን ቢናገሩም በሳተላይት ዲሽ ዘረፋ ሳቢያ የመረጃ ገደብ መፈጠሩ የነጻነት ትግሉን የበለጠ ያፋፍመዋል ሲሉም ገልጸዋል። አክለዉም የኢትዮጵያ መንግስት እየፈጸመ ያለዉ አፈና፣ዘረፋ፣ማፈናቀል፣ማሰር፣መግደል ከኢትዮጵያ ህዝብ ያልተሰወረ በመሆኑ ክእንግዲህ በሗላ ነጻነታችንን በድል ለመቀዳጀት ቁርጠኝነታችንን ማዳበር እንጂ በሳተላይት ዲሽ ዘረፋ የምንገታ አይደለንም ብለዋል።
No comments:
Post a Comment