Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 5, 2015

አርበኞች ግንቦት7 በኦሮምያና በጎንደር የተፈጸሙትን ግድያዎች አወገዘ

በተለያዩ የኦሮሚያ ቦታዎች የዩኒቨርሲቲና የሃይ ስኩል ተማሪዎች፣ እንዲሁም ነዋሪዎች ሕግ መንግስቱ የሚፈቅድላቸውን መብት በመጠቀም ተቃዉሞ ላለፉት በርካታ ቀናት እይሰሙ ነው።
ለሕገ፣ ለሕገ መንግስቱ፣ ለሰብዓት ምንም ደንታ የሌላቸው የህወሃት/ኢሕአዴግ ታጣቂዎች ላለፉት 24 አመት ሲያደርጉ እንደነበረው ወገኖቻችንን በጥይት ኤያረገፉ ነው።
ብእር ለያዙ እጆች ሰደፍ፣ ወረቀት ለያዙ እጆች ዱላ ፣ መብትን ለሚጠይቁ አንደበቶች ጥይት ሆኗል መልሱ። አሁንም እንዳለፉት አመታት፣ ኢትዮጵያዉይን በኢትዮጵያዉይንን እጅ ደማቸው እየፈሰሰ ነው።
ወያኔዎች ሶስት ተማሪዎች እንደተገደሉ አምነዋል። ቁጥሩ ግን ከዚያ በላይ እንደሆነ በገሃድ እየተዘገበ ነው።
በነገራችን ላይ ወያኔዎች በኦሮሚያ ብቻ አይደለም ጥይት እያረከፈከፉ ያሉት። በጎንደርም ላለፉት ጥቂት ቀናት ወደ 14 የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎንች በታጣቂዎች ተገድለዋል።
ወገኖች እነርሱ ላለፉት 24 አመታት ሲገድሉ ነው የኖሩት። በዘር ከፋፍለዉን እንዳንግባባ አድርገዉናል። “እነርሱና እኛ እንድንባባል” አድርገዉናል። ካልነቃን፣ ካልተስማማን፣ ካልተባበርን፣ እነርሱ ምንም የሚሆኑት ነገር የለም። አሜሪካኖችና ምእራባዉያን ያዝኑልናል ብለን የምናስብ ከሆነ ደግሞ በጣም ተሞኝተናል። ተለያይተን ባለንበት ሁኔታ ምንም የሚሻሻል ነገር አይኖርም። ለትንሽ ጊዜ ጋብ ብሎ ከወራት፣ ከአንድ አመት በኋላ ደግሞ እንደገና ዜጎች ተገደሉ የሚል ዜና እንሰማለን።
እንግዲህ ነጻነት በፉከራና በንዴት አይመጣም። መሰባሰብ ያስፈልጋል። ተግሉን በግብታዊነት ሳይሆን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል። ለዚህ የፖለቲካ ልዩነቶች አሉን፣ በተቻለ መጠን ባሉን ልዩነቶች በሰለጠነ መልኩ መከራከራችን እና መወያየታችንን እየቀጠልን፣ በምንስማማባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ግን የጋራ ትግል ማድረግ እንችላለን። ለዚያም መስራት አለብን።
ከዘር አጥር ወጥተን፣ ፣ ወያኔዎች በማካከላችን ያስቀመጡትን የዘረኝነት ነቀርሳ ነቅለን፣ ኦሮሞ፣ ይሁን ትግሬ፣ ጉራጌ ይሁን ከንባታ፣ ጎንደሬ ይሁን ጎጃሜ፣ ሙስሊም ይሁን ክርስቲያን ሁላችንም እኩል የሆንባትን አገር ለማየት፣ በአዲስ መንፈስ እንነሳ። እንዲህ መቀጠል የለበትም። አንድ በአንድ እኮ እያለቅን ነው !!!!!!
ከዚህ በታች የምታዩት ወያኔዎች በወገኖቻችን ላይ ሰሞኑን ያደረሱት ነው !!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials