በምስራቅ ጎጃም ነዋሪ የሆኑ #ወጣት_ሴት የአማራ ብሄር ተወላጆች በኦሮሞ ወንድምና እህቶቻቸው ላይ እየደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ ሀዘናቸውን በመግለፅ ዲርጊቱን እየፈፀመ ያለውን የመንግስት ተላላኪ የሆነውን ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት በማውገዝ ወገናችን የሆነው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የሆነው የፍትሀዊነት የነፃነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች የአማራው ህዝብ ጥያቄም በመሆኑ እንደሚጋሩት ገልፀዋል። የኦሮሞ ህዝቦች በጀመሩት ትግል የአማራው ህዝብም አብሮ ተሰልፎ እንዲታገል ጠይቀው እነሱም ከትግሉ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም የአማራውን ህዝብ ሆን ተብሎ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ለማጋጨት የሚሰራውን ደባ በማጋለጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ እንዲተባበርና በጎንደር ላይ በፖለቲክስ አሻጥር ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት ላይ ያለው ስርዓት ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ጠይቀው ለሱዳን ሊሰጥ ሽር ጉድ እየተባለለት ያለውም የኢትዮጵያ መሬት ከህዝብ እውቅናና ፍላጎት ውጪ መሆኑን ገልፀው የህወሀት/ ኢህአዲግን ስርዓት ለማስወገድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በአንድነት እንዲረባረቡ ጠይቀዋል
No comments:
Post a Comment