Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, December 13, 2015

ሰልፈኞች በምዕራብ ሸዋ ግንደበረት የመለስ ዜናዊን ፓርክ በእሳት አነደዱት – አጋርፋና ወሊሶ በተኩስ ድምጽ ተናውጠዋል




(ዘ-ሐበሻ) እየተካረረ የመጣውና በኦርሚያ ክልል ትናንሽ ከተሞችን ጨምሮ እየተደረገ ያለው ሕዝባዊ ቁጣ በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በአቡነ ግንደበረት ደርሶ በዚሁ ከተማ ውስጥ ያለውንና ካለ ሕዝቡ ፍላጎት በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ስም ተሰይሟል ያሉትን ፓርክ አቃጠሉት::
abune gindeberet
በምእራብ ሸዋ አቡነ ግንደበረት ከተማ የሕዝቡ ቁጣ ገንፍሎ ከወጣ ወዲህ በስፍራው የተሰማራው የአጋዚ ኮማንዶ እንኳ ሊያስቆመው እንዳልቻለ የገለጹት ምንጮች ፓርኩን የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊን ስም በእርግማን መልክ እያነሱ ሲያቃጥሉት እንደነበር ምንጮች ዘግበዋል::
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአምቦ አሁንም አለመረጋጋቱ ያለ ሲሆን በወሊሶ ዛሬም በተፈጠረው ግርግር ሰዎች እየሞቱ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል:: በወሊሶ ንግድ ቤቶች ሱቆቻቸውን ዘግተዋል:: አካባቢው በተቃውሞ እና በአጋዚ ጦር ጥይት ተናውጣለች::
በአጋርፋም ከፍተኛ ተቃውሞ መነሳቱ ተሰምቷል:: አካባቢው በጥይት ድምጽ እየተናወጠ ነው::

No comments:

Post a Comment

wanted officials