ይሁንና የኢትዮጲያዊያኑን በገፍ መጨፍጨፍ የወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ቢሰሙም ለግድያው ትኩረት አለመስጠታቸው ታውቋል፡፡እዲያውም ይባስ ተብሎ የሰሜን ጎንድር ዞን ገዢ አቶ ግዛት አብየ ሟቾቹ በህገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው የገቡ ናቸው በማለት ሃዘኑን እጥፍ ድርብ እንዳደረገው እየተገለፀ ነው፡፡
ቢሆንም ግን መተማ እና አካባቢዋ ውጥረት ነግሷል፡፡የወያኔ ባለስልጣናት የኢትዮጲያን መሬት ለሱዳን አሳልፈው ለመስጠት ሽርጉድ እያሉ በሚገኝበት ዋዜማ የጅምላ ግድያው መፈፀሙ የአካባቢውን ህዝብ ይበልጥ እንዳ ስቆጣው ለማውቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment