Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 12, 2015

“ብልታችንና የሴቶቻችን ጡት በፒንሳ እየተጠመዘዘ በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ከተሰቃየን በኋላ ተባረናል”

የሸዋ ኦሮሞ አማሮችን እየጨፈጨፈና እየመነጠረ ነው(ኢሰመጉ)

በዘመናዊት ኢትዮጵያ ከዘመነ ሚኒሊክ እስከ ደርግ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት ተወላጆች በበለጠ በሃገሪቱ ላይ የስልጣንና የፈላጭ ቆራጭነት ሚና ባለቤት የነበረው የሸዋ ኦሮሞ ጨቋኝና ወራሪ በሚል አማራን እየጨፈጨፈ ነው። ይህ የኢሰመጉ ሪፖርት በሸዋ የሚኖሩ አማሮችን አሳዛኝ የመከራህይወት ፍንትው አድርጎ ያጋለጠ ነው።
~———–~———–~—–—–~———-~—–
“ብልታችንና የሴቶቻችን ጡት በፒንሳ እየተጠመዘዘ በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ከተሰቃየን በኋላ ተባረናል” ከምዕራብ ሸዋ የመጡ የአማራ ተወላጆች
December 3, 2015
ሰሚ ያጣው የሰመጉ ጩኸት
( በሙሉቀን ተስፋው )

ሰብአዊ መብት ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ስደርስ ቤቱ በጋዜጠኞችና በውጭ ዲፕሎማቲክ ቡድን ተወካዮች ተሞልቶ ነበር። ሰመጉ “ብሔር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት እንዲሁም በልማት ስም በዜጎች ላይ የሚፈጸም የማፈናቀልና የንብረት ማውደም በአስቸኳይ ይቁም!” በሚል ያዘጋጀውን መግለጫለመስማት ነበር። ከአፋር ክልል መንግሥት የቴምር ዛፍ የወደመባቸውንና በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ሀብት ንብረታቸው ተቃጥሎ የተባረሩ አማራ አርሶ አደር ተወካዮችን ጭምር በማስመጣት ምስክርነት እንዲሰጡ ፊት አካባቢ ተቀምጠዋል። የተለያዩ የሰመጉ የሥራ ኃላፊዎች መግለጫውንካነበቡ በኋላ ከሁለቱም ቦታ የመጡ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የነበረውን ሁኔታ ሲናገሩ የሚያሳዝንም ተስፋ የሚያስቆርጥም ነበር።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ የአማራ ተወላጆች የተለያየ ዓይነት ሰብሎችን በመዝራት ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና ክልሉን በአጠቃላይ ለአገሪቱ ገበያ የሚቀርብ ምርት በማምረት የሚታወቁ ውጤታማ አርሶ አደሮች ነበሩ። ይሁንናበአካባቢው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የጸጥታ ኃፊዎች እነዚህን አርሶ አደሮች “እናንተ የዚህ አካባቢ ተወላጅ ሳትሆኑ ሀበት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጅ ግን ከእናንተ ያነሰ ገቢ ያላቸው ናቸው፤ ይህን ገቢ ያገኛችሁት በእኛ መሬት ላይ ነው፤ ስለዚህ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉንለቃችሁ ውጡ” በማለት ንብረታቸውን በተለያየ ጊዜ በመንጠቅ እነዚህን አርሶ አደሮች በተለያየ ጊዜ ለእስራት ዳገዋቸዋል። የአካባቢውን ሕዝብም “በእናንተ መሬት ነው ሀብት ያፈሩት” እያሉ ጥላቻና ግጭትን ሲሰብኩ እንደቆዩ በሰመጉ በ136ኛ መግለጫና ምስክርነታቸውን በሰጡ አርሶ አደሮችተነግሯል።
ምስክርነታቸውን ከሰጡት መካከል በአካባቢው ተወልዶ ያደገው አቶ አለሙ አስፋው “በ1996 ዓ.ም. በዞኑ መዳሉ ወረዳ 52 እንዲሁም በ2002 ዓ.ም. ደግሞ በዳኖ ወረዳ 152 የአማራ ቤትና ንብረት ሲቃጠል ምንም የተወሰደ እርምጃ የለም” ሲል ከዚህ በፊትም ስለነበረው ብሔር ተኮር ጥፋትይናገራል። የሰመጉ መግለጫና ገበሬዎቹ እንደሚያረጋግጡት መጋቢት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. አቶ ዘውዱ እንዳለ የተባለ የኦሮሞ ተወላጅ ተገድሎ ይገኛል። ተገድሎ የተገኘውን ገዳይ ሁሉም ኀብረተሰብ ወንጀለኛውን ለማገኘት እየተረባረበ ባለበት ሰዓት “ይህ ግድያ የተፈጸመው በአማራ ብሔርተወላጆች ነው” በማለት የኖኖ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኃይሉ ድሪባ፣ የኖኖ አሎ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ጎሳየ ገችና መቶ አለቃ ገነነ በየነ የተባሉ የፖሊስ አባላት የቀበሌና የፖሊስ አባላትም በማስተባበር የአካባቢው ሕዝብ በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ እንዲነሳሳ በማድረግሚያዚያ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. 85 አርሶ አደር አባውራዎችን ለእስራት ከዳረጓቸው በኋላ ቅዳሜ ማለትም ሚዚያ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት አካባቢ ዘር በመምረጥ የአማራ መኖሪያ ቤትና ንብረት ነው ያሉትን እየመረጡ በእሳት እንዲቃጠል አድርገዋል።
የታሰሩትን ወንዶችና ሴቶችም ብልታቸውንና ጡታቸውን በፒንሳ እየጠመዘዙ ቤቱን ለሚቃጠልበት የሚውል ለነዳጅ በማለት ከእያንዳንዳቸው 300 ብር ተቀብለዋቸዋል። ከ27 ገበሬዎች ብቻ 8100 ሰብስበዋል። ገበሬዎቹ ሲወጡ ሀብት ንብረታቸውም ሆነ የነበራቸው ነገር ሁሉ ወድሞ ነውያገኙት። በንግድ ሥራ የምትተዳደር ወ/ሮ ጽጌ የተባለች የአካባቢው ነዋሪ የነበረውን ሁኔታ ስትገልጽ “ቤታቸው ሲቃጠል ልብሳቸውን ሁሉ አጥተው ራቁታቸውን ደብቂን እያሉ ወደኔ በርካታ ልጆች መጡ። ማጀት አስገብቼ ወደ ፖሊስ አዛዡ ቢሮ በመሄድ ‹ኧረ ተው በሰው ስቃይ እንዲህአትደሰት?› ስለው ገና አንቺም ትቃጠያለሽ አለኝ” በማለት የነበረውን ሁኔታ ትናገራለች።
አቶ ዓለሙ አስፋው በበኩላቸው “የሚሊሻ ኮማንደር ነኝ። በጊዜው ሰላሳ ጎራሽ ክላሽ ይዤ ነበር። የፖሊስ አዛዡ አቶ ደመና ግዘውን ሲገድላቸው ቆሜ እየተመለከትኩ ‹እንዴ ተው ሕግ ባለበት አገር› ስለው ‹አማራ እኮ ነው አይመለከትህም› አለኝ፤ በያዝኩት ጠመንጃ አይደለም እርሱን 30 ሰውምመግደል እችል ነበር፤ ግን ያን ባደርግ የሁሉም ችግር መንስኤው እርሱ ነው ስለምባል እያነባሁ ዝም አልኩ፤ እኔ ሰላም ለማስከበር ላይቤሪያ ድረስ ሄጃለሁ፤ ሆኖም በአገሬ ሰላም የለም። የሰው አገር ሰላም ሳስከብር በአገሬ ላይ ግን ስለሰላም መናገር እንኳን አልቻልኩም” ሲል በምሬት ገልጿል።
አቶ ደመና በሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ልጃቸውን ሊድሩ ዘመድ አዝማድ ሁሉ ተጠርቶ ዝግጅቱ ሁሉ አልቆ ነበር። ሆኖም የልጃቸውን ደስታም ሳይመለከቱ ሰርጉ አንድ ቀን ሲቀረው በመንግሥት የፖሊስ አዛዥ ተቀጥቅጠው ሞተዋል። የሟች ወንድም “ወሊሶ ሆስፒታል ሳይደርስ ነውየሞተው፤ የግፋቸው ግፍ ራሳቸው የገደሉትን አስከሬን ለምርመራ አዲስ አበባ መላክ አለብን ብለው 6000 (ስድስት ሽህ ብር) አምጣ አሉኝ። የለኝም ስላቸው አስከሬኑን አውላላ ሜዳ ላይ አስቀምጠው መውሰድ እንደማልችል ተነገረኝ። አስከሬኑ ሜዳ ላይ ፈራርሶ ከሚቀር በማለት ተበዳድሬሰጠው። የራሴን እንኳ እንዳልሰጥ ያለኝን በሙሉ አቃጥለውታል። የግፍ ግፍ ነው የተሰራብን” በማለት በእንባ ነው የተናገሩት።
ሰመጉ በ136ኛ መግለጫው የአንድ ሰው ማለፉን፣ 10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ 99 የእሳር ክዳን ቤቶች በእሳት መቃጠላቸውንና 25 የቆርቆሮ ክዳን የመኖሪያ ቤቶች በእሳት መውደማቸውን ገልጿል። የአርሶ አደሮቹን መኖሪያ ቤትና ንብረት ቃጠሎ ተከትሎ ከፍተኛቁጥር ያላቸው ሴቶች፣ ሕጻናትና አቅመ ደካሞች የሚገኙባቸው ተፈናቃዮች በአካባቢው በመሰደድ ወደ ደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አበሸጌ ወረዳ ድንኳን ውስጥ ተጠልለው ሲረዱ መቆየታቸውንም አስታውሷል። ሰመጉ በጋዜጣዊ መግለጫው ጥፋት የፈጸሙት የመንግሥት አካላት ምንም አይነት ሕጋዊእርምጃ እስካሁን እንዳልተወሰደባቸውና የተፈናቀሉ ገበሬዎችም ተመልሰው በሰላም መኖር ለመቻላቸውን ጠቅሷል። ይባስ ብሎም ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሮንድ እንዲጠብቅ የተመደበውን አቶ አቢ ተክለማርያም በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል። ገበሬዎቹ እንደሚናገሩት ከሚለብሱት ልብስጀምሮ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስጠጓቸው የአካባቢው ሰዎች እንደሰጧቸውና ተመልሰው ግን ለመኖር እስካሁን አዳጋች እንደሆነባቸው ነው ለዝግጅት ክፍላችን የገለጹት።
በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በጥይት ተደብድቦ የተገደለውን አቶ አቢን ተክለማርያምን አገዳደል በተመለከተ ሲናገሩ “የሌሊት ጥበቃ ሮንድ ከአራት ኦሮሞዎች ጋር ተመደበ። ሆኖ ተብሎ እንደዚህ እንደተመደበ የሚያውቀው ነገር አልነበረም። ነገር ግን በጥይት ተደብድቦ ተገደለ” በማለት የተሰራውን ሴራይገልጻሉ። እንደአርሶ አደሮች ገለጻ ከሆነ ይህን በዋናነት ሲያስተባብሩ የነበሩ የኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት ሕጋዊ እርምጃ አልተወሰደባቸውም። አርሶ አደሮቹም የወደመባቸው ንብረት ሊሰጣቸው ቀርቶ ተመልሰው እንኳን ሕጋዊ መሬታቸውን ለማልማት እንዳልቻሉ ነውየሚገልጹት። በተያያዘም በአፋር ክልል በአሳይታ ወረዳ ዋሙሌ ቀበሌ በስኳር ኮርፖሬሽን ለሸንኮራ አገዳ ልማት በሚል የቴምር ዛፍ የወደመባቸው ከፊል አርብቶ አደሮችን ሕይወት አመሰቃቅሏል። የተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክት የነዋሪዎቹን ፈቃደኛነት ሳይጠይቅ ካሳም ሳይፈጽም ከ8300 በላይየቴምር ዛፎች እንደተመጠሩና ነዋዎቹም ችግር ላይ መሆናቸውን ሰመጉ በ138 ልዩ መግለጫው ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ችገሩ አለመቆሙን ነው በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ የተደረገው። ከአፋር ክልል የመጡት ነዋሪዎች እንደሚሉት “አካባቢውን ለቀን ወደ ጅቡቲናሶማሊላንድ እንድንሰደድ ይፈለጋል። እኛ ግን የምንሄድበት የለንም። የምንመገበው ቴምር ነው፤ ለቤት መሥሪያና ለመኝታም የምንጠቀመው የቴምር ዛፍን ነው፤ ሆኖም አሁን ሁሉም እንዳልነበር ሆኗል” ሲሉ ገልጸዋል። ሰመጉ በ138 ልዩ መግለጫ የአፋር ባህልን መሠረት በማድረግ አንድ የቴምርዛፍ ሲቆረጥ ካሳ የሚሰጠው ሰባት የቁም ከብት እንደሆነ ጠቅሷል። ሆኖም ነዋሪዎቹ እስካሁንም ምንም ዓይነት ክፍያ ካለማግኘታውም ባሻገር አቤቱታቸውንም የሚሰማቸው አካል ማጣታቸውን ጭምር በምሬት ገልጸዋል።
(ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው ሰመጉ ሕዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሁም 136ኛና 138 ልዩ መግለጫዎቹን መሠረት በማድረግ ነው)
source

No comments:

Post a Comment

wanted officials