ፎቶ ከፋይል
(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳው የሕዝብ ቁጣ ወደ ተለያዩ ከተሞች እየተዛመተ ሲሆን የመንግስት ሚድያዎች በበኩላቸው ምንም እንዳልተፈጠረ መረጃዎቹን በማፈን ስለ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እያወሩ ይገኛሉ::
በሃሮማያ ዪኒቨርሲቲ የተማሪዎቹን ሰላማዊ ጥያቄ ፖሊስ በኃይል ለመበተን ባደረገው ጥረት ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸውን ዘ-ሐበሻ ቀደም ብላ መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን ይህን ተከትሎም በባሌ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ አመሻሹ ላይ ተማሪዎች ቁጣቸውን መግለጻቸው ተሰምቷል::
በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ቁጣቸውን ከገለጹ በኋላ ወደ መኝታቸው እንደሄዱ የገለጹት ምንጮቻችን በተለይ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ በመንግስት ኃይሎች የተወሰደውን እርምጃ ተቃውመዋል::
መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚገኝ የሚገልጹት ምንጮች አካባቢው በፖሊስ መወረሩም ተዘግቧል::
No comments:
Post a Comment