በተያያዘ ዜናም የአዳማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የተቃውሞ ስልት በመቀላቀል በተግባር ማዋላቸዉ ታዉቁአል። በሂደቱም ተማሪዎቹ በጊዜ ወደ መመገቢያ ካፌ በመሄድ ወረፋ ይዘው የገቡ ሲሆን ምግባቸውን ከተቀበሉ በሁዋላ በአንድነት በከፍተኛ ድምፅ በማሰማት 15 ሚሊዮን ወገናችን በረሀብ እየተሰቃየ እያለ ፣ ሚሊዮኖች ከቀያቸው እየትፈናቀሉ ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች በየማጎርያ ካምፑ ተግዘው በእስር ላይ ሳሉ ፣ ወገኖቻችን በጅምላ እየተጨፈጨፉ እኛ ከወገኖቻችን ተነጥቆ የሚቀርብልንን ምግብ አንበላም በማለት ምግቡን ጠረጴዛው ላይ እንዳስቀመጡት ሳይነኩት ጥለው መዉጣታቸው ታዉቁአል።
እንቅስቃሴው ሰላማዊ በሆነ መንገድ ወደ ተለያዩ ከፍተኛ ተቁአማት እየተዛመተ መሆኑን ታዉቁአል። እንቅስቃሴው በኦሮሞ ተማሪዎች በማስተር ፕላኑ ዙሪያ ቢጀመርም፣ መልኩን በስፋት ቀይሮ፣ አሁን የሁሉም ዜጎች እንቅቃሴ ሆኗል። የመሰረታዊ የመብት፣ የነጻነት የእኩልነትና የዲሞክራስ ጥያቄ ሆኗል።
በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች እየተደረጉ ያሉ እጅግ በጣም ብዙ እንቅስቃሴዎች እንደተጠበቁ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ በሃረር ከተማ (ሃረሬ ክልል)፣ በዲላ ( ደቡብ ክልል፣ ጌዲዮ ዞን ዋና ከተማ) እንዲሁም በአዋሳ (የደቡብ ክልል ዋና ከተማ) ተቃዉሞዎች ተደረገዋል።
No comments:
Post a Comment