Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 1, 2015

መምህር ግርማ ሌላ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው


ፖሊስ ሰው በመግደል ወንጄል እጠረጥራቸው በማለት ባቀረበው ቁጥር ሶስት ክስ መምህር ግርማ ተጨማሪ 14 ቀን በእስር እንዲቆዩ ፍርድቤቱ ትእዛዝ በመስጠት ወደ እስር ቤት መልሷቸዋል። በጠቅላይ ቤተክህነት አጥብቀህ እሰርልኝ ባይነት በኘንግስት አስፈጻሚነት በእስር የሚገኙት መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ፀሎት ደማሚታቸው ፣ ፣ ፀበል ጠላት ሰይጣንን መግረፊያቸው ብቻ መሆኑ እየታወቀ ።ህንጻ እግዚአብሔርን በማፍረሰ ሰው በመግደል ወንጄል መክሰስ የሚገርም ነው።በእውኑ እኒህ አባት ነበስ ገዳይ ወንበዴ ነበሩ ? አገልግሎታቸውን በቤተክርስቲያን ቅጥር ሲፈጽሙ የነብሰገዳይ ተግባር ነበር የሚሰሩት? ጉባኤያቸውን የተሳተፈ ሁሉ ይታዘበናል ማለት ተገቢ ነበር።
ሆን ተብሎ በድፍረት ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በማሳዘን ሰይጣንን ደስ ለማሰኜት የሚደረገው የመንግስት እና የጠቅላይ ቤተክህነት ጥምር ደባ አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን ሰይጣን የቱን ያህል አለምን እንደተቆጣጠረ አጉልቶ የሚያሳይ ነው።
እዚህ የምኖርበት ሀገር ለሰይጣን ሀዋልት ተሰራ ብዮ ሲደንቀኝ ለካስ በተወለድኩባት ሀገር ፣ ያውም እነ ሰማዐቱ አቡነ ጴጥሮስ እነ ቅዱሱ አቡ ተ/ ኃይማኖት በተቀመጡባት የጠቅላይ ቤተክህነት ወንበር የሀሰት አርቲፊሻልጺሙን አስረዝሞ ሰይጣን በገሀድ ቁጭ ብሎ ገዳማት ሲፈርሱ፣ መነኮሳት ሲደበደቡ በርሀብ ሲሰቃዪ እሰዪው እያለ ቤተክርስቲያናችንን በግልጽ እና በስውር ማዳከሙን ተያይዞታል።

ልያ ፋንታ
ከዋሽንግተን ዲሲ (USA)

No comments:

Post a Comment

wanted officials