አትሌት ፈይሳ ሌሊሴ እንዴት አድርጎ የወያኔን መንግስት አሳሪነት እንዳሳየ እየተደመምን እስቲ ደሞ
አትሌት ዮናስ ክንዴ የተባለ ሌላ ጀግና እንዴት አድርጎ በሪዮ ኦሎምፒክ የወያኔን መንግስት አሳዳጅነት
እንዳጋለጠ እንመልከት።
ጉዳዩ እንዲህ ነው። አለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ በአለም ላይ ተሰደው የሚገኙ ሀገር አልባ ስደተኞችን
ለማስታወሰ እና እነሱንም ወክሎ ከሌሎች ሀገራት እኩል የሚወዳደሩ 43 ሰዎችን በመጋቢት ወር መረጠ። ከነዚህም ውስጥ
ስደተኛ በጣም የሚሰደድባቸው ሀገራት በሚል መስፈርት ከተለዩት ውስጥ ከሶርያ ጀርመን ና ቤልጅየም የገቡ 2፣
ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ወደብራዚል የተሰደዱ 2፣ ከደቡብ ሱዳን ኬንያ ካኩማ የስደተኞች ካምፕ የተጠለሉ 5 አትሌቶችና
ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓዊቷ ሉግዘምብርግ የተሰደደው ዮናስ ክንዴ በድምሩ 10 አትሌቶች ሪዮ ዴጄነሮ ብራዚል
ለኦሎምፒክ ውድድር አመሩ። ከመክፈቻው ዕለት አንስቶ ይዘውት የነበረው የተሰደዱበትን ሃገር ባንዲራ ሳይሆን
አምስቱ ቀለበቶች ያሉበትን ነጩን የኦሎምፒክ አርማ ባንዲራ ነው።የሚወክሉት ሃገር ኣልባ የሆነውን ስደተኞችን ነው።
Refugee Olympic Team/ROT/ በሚል መጠሪያ።
ቀውሱ በጣም ከፍተኛ ከሆነባቸው ከሶርያ አትሌቶች ፣ ከደቡብ ሱዳን ከ ደሞክራቲክ ኮንጎ እኩል የዚህ ትውልደ
ኢትዮጵያዊ በሰደተኛች ቡድን መታቀፍ ሲዘገብ ከረመ። በአንጻሩ ከትዮጵያ የተሰደዱ ወገኖች ያሳደዳቸው ምክንያት
ከእነዚህ ሶርያዎች ወይም ደቡብ ሱዳኖች እኩል እንደሆነ ታየ። የወያኔው መንግስት እንደ ኮንጎዎቹ ዘረኛና እኩይ
መሆኑ ተመሰከረ።
በዉሃ ዋና ትግሬ በመሆኑ ብቻ ተመርጦ ዉሃ ውስጥ ያዋረደን የሮቤል ጉዳይ በአለም ሚዲያ ሲዘገብ ከሰደተኞቹ
ውስጥ ሁለቱ ሶርያውያን ራኒ ኣኒስ እና ያሱራ ማርዲኒ በሴቶች ውሃ ዋና ተወዳዳሪ ነበሩ።በአስራ ሰባት አመቷ
ከሶሪያ ተሰዳ ከእህቷ ጋር በባህር ሊሰምጡ የነበሩ 20 ሌሎችን በዋና ጠበቧ ታድጋ ጀርመን በርሊን የደረሰችው
ይችው የሰደተኞች ተወካይ አትሌት ተንደላቆ ተዳልቶለት በ አባቱ ዳኝነት ከተመረጠው የሕወሃቱ ቦርጫም ዋናተኛ
ሮቤል የበለጠ ተዘግቦላታል።ስደተኞች ተዘግቦላቸዋል። ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ረፐብሊክ ወደ ብራዚል
የተሰደዱት ሁለቱ በጁዶ ስፖርት ሲሳተፉ ፣አምስት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሩጫ ሲወዳደሩ ሁሉ የኢትዮጵያ ስም
በስደተኛ አበርካችነቷ እየተጠራ ነበረ። እነ ፈይሳ ሌሊሴ በሪዮው ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ አትሌቶች ተብለው ሰማቸው
ሲተዋወቅ ዮናስ ክንዴ ከኢትዮጵያ ግን በሃገር አልባ ስደተኞች ማልያ በማራቶን ተሰለፈ። ሁለት ኢትዮጵያውያን
አንዱ በመንግስት ተወክሎ አንዱ በመንግስት ተፈናቅሎ። ዞሮዞሮ ኢትዮጵያን ወክሎ ሁለተኛ የወጣው አትሌት እሱም
ሰደተኛነቱን አስመሰከረ የታሰሩ የተገደሉ የኦሮሞያ የጎንደር ወገኖቹን ደም ሲቃ እያየ ወደ ወያኔው የአትሌቶቹ
ካምፕ መሄድ አልወደደም። በይፋ የለም ህዝብ በሙሉ በትኩረት እያየው ኢትዮጵያውያን ታስረዋል አለ። የኢትዮጵያ
መንግስት አሳዳጅነት እና አሳሪነት ወትሮዉኑም ሲታወጅ የቆየ ነው አሁን ሰበብ ተገኘ።
ኤስቢ ኔሽን የተባለው የዜና አውታር <<
Bringing athletes from war-torn countries to Rio>> በጦርነት ከፈረሱ
ሃገሮች የመጡ አትሌቶች በሚል ርዕስ ስር ነሃሴ መጀመሪያ ሳምንት ላይ ያወጣውን ሃተታ በማየት ብቻ
እንደምንረዳው ከሶርያ ፣ከደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ እኩል ኢትዮጵያም በጦርነት ስር እንዳለች ለ አለም አስነብቧል።
የተባበሩትን መንግስታት የስደተኞች መስሪያ ቤትን ጠቅሶ ኤስቢ እንዲህ ሲል << The civil
war in Syria has been driving an outright refugee crisis in Europe. The
United Nations Refugee Agency says there are 4.8 million Syrian
refugees, plus an estimated 8.7 million people displaced inside Syria
this year. Its count of refugees and asylum-seekers from South Sudan is
850,000. In the Democratic Republic of the Congo, it is more than
384,000 refugees and more than a million internally displaced persons.
There are more than 700,000 Ethiopian refugees. This is just a
sampling.>> ሰባት መቶ ሺ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሉ የሚለው ይሄ የመጨረሻው አረፍተ ነገር
የወያኔን መንግስት አጋኖ አጋለጠው እንዳንል እነ ቢቢሲ ሲኢኤን ኤን ኣልጀዚራ ወዘተ የተባሉት ዝነኛ ሚድያዎች
ሳይቀሩ ኢትዮጵያን ከጎንደር ኦሮሚያ አመጽ እስከ ሪዮ ኦሎምፒክ የ አትሌቶች አመራረጥ አድልዎ እያብጠለጠሉ
የመንግስትን ሙስና ሲዘግቡ ነበሩ።
በተለይ የሶርያ ቀውስ ጉዳይ አለም ኣቀፍ አጀንዳ ከመሆኑ ጋር እና ሁለት ሴት አትለቶቹ በዉሃ ዋና ሪዮ
ኦሎምፒክ ላይ ከተሳተፉ ቀን ጀምሮ የእያንዳንዱ ስደተኛ አትሌት የስደት መንስኤ በስፋት ተራግቧል። በሁሉም ዜናዎች
የኛው አትሌት ዮናስ ክንዴ በፖለቲካ ምክንያት ከሃገር መባረሩን እና ለአትሌቶች ምቹ መንግስት እንደሌለ የገለጸው
ለመላው አለም ህዝብ አይን እና ጆሮ ደርሷል።
በሉግዘምብርግ በታክሲ ሹፌርነት ኑሮውን የሚገፋው የ36አመቱ ዮናስ 2ሰዓት ከ17 ደቂቃ ምርጥ የማራቶን
ሰዐቱን በፍራንክፈርት በግል ያስመዘገበ ሲሆን በሪዮው ኦሎምፒክ ዘጠናኛ ወጥቶ ስደተኞች ከማንም እንደማያንሱ
አትሌቶችን ወክሎ የተናገረው ይጠቀስለታል።
ታዋቂው ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አስሩ አትለቶች ከ ስልሳ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በ አለም ላይ የተበተኑ ስደተኞችን ይወክላሉ ሲል ከአስሩ ስድስቱ ወንዶች አራቱ ሴቶች
ሲሆኑ ሁሉም በሃገራቸው ባለ ግጭት የተነሳ የተሰደዱ ናቸው
በማለት የአሜሪካው ኒውዮርከር ድረገጽ ደሞ አትቷል። ኢትዮጵያዊው ዮናስ ክንዴ ከ ኢትዮጵያ የተሰደደው በ2013
ሲሆን በዛ ወቅት አስከፊ ግጭት ነበረ ካለ በአሁን ሰኣት ደሞ ያለውን ጄኖሳይድ ምን ብሎ ህወሃትን
እንደሚያብጠለጥለው መረዳት አይከብድም ።
http://www.newyorker.com/news/sporting-scene/the-refugee-olympians-in-rio
The ten team members—six men and four women—were announced in June
. All have fled conflicts in their home countries.
There are two swimmers from Syria, two judokas from the Democratic
Republic of Congo, a marathoner from Ethiopia, and five middle-distance
runners from South Sudan.
ህወሃት ወያኔ በሁሉም ቦታ ተዋረደ አይቀናውም። በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው አብዮትም በውጪ ሀገራትም። በሃገር ውስጥ ህዝቡ
በአንድነት ተነስቷል። ከእንግዲህ ዘረኛ መንግስት ይብቃን ፋሺስት ወያኔ ይወገድ ብሏል ከጫፍ እስከ
ጫፍ።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለህወሃት ያደሩ ካድሬዎቹ አምባሳደሮቹ ሳይቀር የወያኔን ኤምባሲ ከድተው ለቀዋል።
ህወሃት በየፊናው እየተፍረከረከ ስለመሆኑ ከነሱም ምስክር ሞልቷል። በውጭው ሃገራትም የህወሃት መንግስትን
የሚያወግዙ ሰልፎች በኢትዮጵያውያን እየተስተጋባ ነው።
ሌላው የአለም ህብረተሰብም ገመናውን ከተረዱት ቆዩ። ከነዚህም የተባበሩት መንግስታት ሰሞኑን በ አማራ
ክልልና እና ኦሮሚያ ክልል በግፍ ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን አጣሪ ኮሚቴ ይመደብ ማለቱ ፥ ግድያውንም እነ ቢቢሲ
እና ሌሎች ተደማጭ ሚዲያዎች እያሳበቁት መሆኑ የሚጠቀስ ሲሆን የ አለም አይንና ጆሮ በሙሉ ወደ ብራዚሉ ኦሎምፒክ
ትኩረት ባደረገበት ወቅት ላይም የዚህን አምባገነን መንግስት አሳሪነት በማራቶን ሁለተኛ የወጣው አትሌት ለሊሳ ፈይሳ
እጁን በማሳየት ተናግሯል። እየደጋገመ የዘገበውም ይሄንን ነው።
የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በዚህ አመት ጀመረው ይሄ የ አለም ስደተኞችን ራሳቸውን ወክሎ ማወዳደር
የሚበረታታ ተግባር መሆኑን በመቶዎች የሚቆጠሩ አለም አቀፍ ሚዲያዎች አድንቀውታል። በዛው ልክ የተጠቀሱት ሃገራት
ሶርያ፣ደቡብ ሱዳን፣ዲ አርሲ፣ ኢትዮጵያ ያለባቸው የመንግስታት ችግር ሙስና በመላው አለም ታውቋል።
በዘንድሮው ኦሎምፒክ ከምንግዜውም በተለየ ህወሃት አንገቱን የደፋበት ሆኖ በማለፉ ደስ ይለናል።
እስከመጨረሽው ህወሃትን በአለም አቀፉ መድረክ እናጋልጣለን
ዘአብርሃም ከጀርመን