“ስማችን በጣም እላይ ነው ያለው፡፡ ተፈላጊነታችን በጣም ጨምሯል” ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ትናንት ከተናገሩት የተወሰደ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትናንቱ ስብሰባ ላይ የትምክህተኝነትና ጠባብተኝነት አስተሳሰብ አሁንም በሃገራችን መኖራቸውን ገልጸው በተለይ በተማረው ክፍል አካባቢ “ብቅ ጥልቅ” እንደሚሉ አጽንኦት ሰጥተውታል፡፡ በዜናው ላይ ተቆራርጦ እንደቀረበልን ከሆነ በዋናው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተናገሩት ግን እንዲያው በሽርክቱ ነበረ፡፡ (አሁንም ትምክህተኛ እና ጠባብ እያሉ ህዝብን መሳደብ ግን የትም አያደርስም፡፡)

በተጨማሪም አብዛኛው አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ስርዓቱ “የአድልዎ ስርዓት” እንዳልሆነ እና “የብሔራዊ
ጭቆና የተወገደበት ስርዓት” እንደሆነ እና ህዝብን አሳታፊ ስርዓት እንደሆነ “የሚያምኑበት ሁኔታ አለ” ብለዋል፡፡
“የሚያምኑበት ሁኔታ አለ” የምትለዋ ሃረግ ቃል በቃል የተወሰደች ናት፡፡ ሃረጓ ጥርጣሬን uncertainty በውስጧ
ያዘለች ይመስላል፡፡ አምነዋል ወይስ አላመኑም?
እኔን የገረሙኝ ከላይ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ያስቀመጥኳቸው ቃል በቃል የወሰድኳቸው ሌሎቹ ሁለቱ ሃረጎች ናቸው “የአድልዎ ስርዓት” እና “የብሔራዊ ጭቆና የተወገደበት ስርዓት” የሚሉት ሲሆኑ ሰውየው ሳያስቡት ውስጣቸው የሚያብሰከስካቸውን በደመነፍስ ወረወሯቸው እንዴ አስብሎኛል፡፡
በነገራችን ላይ “ኃለማሪያም” እና “ሃይለማሪያም” ልዩነት ይኖራቸው ይሆን? ምን ይታወቃል ይሄም ያስጠይቅ ይሆን ብዬ ነው፡፡ “ሐይለማሪያም” ተብሎ ሲጻፍም አይቻለሁ፡፡ እሳቸው የቱን ይሆን የሚጽፉት?

No comments:
Post a Comment