በፌዴራልና ክልል ከተሞች መንግስታዊ አገልግሎቶች እየተስተጓጎሉ እንደሆነ ተነገረ
ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008)
በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ላይ በተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በፌዴራልና ክልሎች መደበኛ መንግስታዊ አገልግሎቶች በመስተጓጎላቸው የህዝቡን ምሬት እያባባሱ እንደሆነ ተገለጸ።
አዲስ አበባን ጨምሮ በፌዴራልና የልል መንግስታዊ ተቋማት በመዘዋወር መረጃውን ያደረሱን የኢሳት ምንጮች፣ በመንግስታዊ ተቋማት ጉዳይ ለማስፈጸም የሚሄዱ ነዋሪዎች አገልግሎት ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ በመፈጠሩ በስርዓቱ ላይ መማረራቸውን ገልጸዋል።
በተለይም በአንዳንድ የኦሮሚያ እና አማራ አካባቢዎች በህዝባዊ እምቢተኝነቱ ምክንያት መንግስታዊ መዋቅሩና ጽ/ቤቶቹ በመዘጋታቸው መደበኛ ስራዎችና አገልግሎቶች ጭምር መቋረጣቸውን ምንጮች ይገልጻሉ። በተለይም በጎንደር፣ ጮሂት፣ ጎርጎራ፣ ቆላድባ፣ ባህርዳር፣ ማጀቴ የመሳሰሉ አካባቢዎች የመንግስት ተቋማት አገልግሎት መስጠት የማይችሉበት ሁኔታ መፈጠሩ ታውቋል።
በየአካባቢው የሚገኙ የመንግስት ሹመኞችና ሰራተኞች ከነሃሴ 8 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ መንግስት የተነተሳብኝን ተቃውሞ ለማርገብ ያስችለኛል በሚል በየአዳራሹ በስብሰባ እየተጠመደ መሆኑን መመልክታቸው ገልጸዋል።
በስብሰባው የመንግስት ሰራተኞች የአካባቢውን ባለስልጣናት እና ካድሬዎችን “ህዝብ አንፈልጋችሁም ብሏል ለምን ስልጣናችሁን አትለቁም?” በሚሉ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን አስጨንቆ እንደያዛቸው ምንጮቻችን በስፍራው በመገኘት ለመታዘብ መቻላቸውን ገልጸዋል።
የየአካባቢው ባለስልጣናት ካድሬዎች ችግሩን የፈጠሩት “የብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት የማይቀበሉ የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” በማለት ውጫዊ ለማድረግ ቢሞክሩም የሰራተኛውን ጆሮ ለማግኘት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችሏል።
በኢትዮጵያ የተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት ተጠናክሮ ሊቀጥልና ሊስፋፋ እንደሚችል ባሳለፍነው ሳምንት የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

No comments:
Post a Comment