Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, August 13, 2016

በቅርብ የኢትዮጵያ ታሪክ፡ትግራይ እሚባል ክፍለ-ሃገር፡ አልነበረም። – ዘርኡ መሃሪ There was no a region called Tigray before 1991




ትግራይ ሳይሆን፡ ትግሬ ጠቅላይ-ግዛት የሚባለው ግን በአጼ ምንሊክ የተካለለ ነው። “ትግራይ” እሚለው ታድያ እንዴት መጣ? የየትኛው አካባቢ መጠርያነበር? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ፡ ብዙ ሰው (ወጣት የትግሬ ክፍለሃገር ተወላጅ ጭምር)የማያቀውን ሃቅ እንደሚከተለው እጠቅሳለሁኝ።


ኤርትራ እሚባል እንዳልነበረ ሁሉ፡ ትግሬ ጠቅላይ ግዛት እሚባልም አልነበረም። ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው፡ በአጼ ምንሊክ ግዜ ነው በጠቅላይ ግዛትነትየተዋቀረው። ልብ በሉ፡ ትግሬ እንጂ ትግራይ አላልኩም። ትግሬ ጠቅላይ ግዛት የሚለው አጠራር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ(በአጼ ኅይለሥላሴም በደርግም ጊዜ)የነበረ አጠራር ነው::


ትግራይ የሚለው አጠራር ታድያ መⶬ ነው የታወቀው? መልሱ በ1928 ወረራ አካባቢ፡በጣልያንና በእንግሊዝ የሚል ይሆናል፡ ከዛ በፊትና በሃላ ትግራይየሚለው ቃል የየትኛው አካባቢ መጠርያ ነበር?

ትግራይ ማለት ብዙ ባላባቶⶭ ያልነበሩበት አካባቢ፡ ከተለያዩ አካባቢዎች(ከኤርትራ፡ ከተቀረው የትግሬ አውራጃዎⶭ) ለከብቶቻቸው ሳር ፍለጋ፡ ወይምበሽፍትነት ሄደው እዛው የቀሩ ሰዎች የሰፈሩበት፡አሁን በትግሬ ክፍለ-ሃገር ሽሬ እና አካባቢው የሚገኘው፤ በሰሜን እስከ ኤርትራ ድንበር፡ በምአራብ እስከ ተከዜወንዝ ያለው ቦታ ነው። አንዳንዴ ሰዎⶭ ዓድዋንም ይጨምራል ይላሉ። በአሁኑ አጠራር፡ ሰሜናዊ ምአራብ እየተባለ እሚጠራው አካባቢ ብⶫ ነበር ትግራይተብሎ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲጠራ የነበረው። ለምሳሌ ያክል ለመጥቀስ፡ አንድ የተንቤን ተወላጅ፡ያኔ፡ ከተንቤን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ለመሄድ ሲነሳ፡ የት ነውእምትሄድው ተብሎ ቢጠየቅ፡ መልሱ (ናብ ትግራይ ኢየ) ወደ ትግራይ ነው እምሄደው የሚል ይሆናል። ተንቤኖⶭ ትግራይ ሲሉ፡ ቀደም ብዬ የጠከስኩትንአከባቢን ነበር እሚያቁት። በዓጋሜ በኩል ቢሆንም ተመሳሳይ ነው። የዓጋሜ ነዋሪዎⶭ ትግራይ ሲሉ፡ ከዓጋሜ በስተ መእራብ ሲሄዱ የሚገኙትን፡ ቀደም ብዬየጠከስኩውⶨውን ቦታዎⶭ ማለታⶨው ነበር። ይሄ እንግዲህ ጸህፊው በሚያቀው፡ በኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ 70ⶩ ድረስ የነበረ ነው። ምሳሌ ልጥቀስ፡ የደርግእድገት በህብረት ዘመⶫ በተጀመረበት ወቅት ነው። በትግሬ ጠቅላይ ግዛት ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ የዘማⶮⶭ ሃላፊዎⶭ፡ ከዓዲ ግራት ተነስተው፡ በላንድሮቨራቸው ፡ወደ ሽሬ በሚያመሩበት ጊዜ ብዘት እምትባል ትንሽ ከተማ ይደርሳሉ። ብዘት እንደደረሱ፡ አንድ መንገደኛ ወደ እነሱ ጠጋ ይልና፡ አፈናጥጡኝሲል ይጠይቃቸዋል። እነሱም፡ ወድየት ነው እምትሄደው ብለው ቢጠይኩት ወደ ትግራይ ሲል መለሰላቸው። ትግራይ ያለው ሽሬ አካባቢ ማለቱ ነበር።

እንግዲህ የህዝቡ ስሜትና ኩራት በአውራጃ የተመሰረተ ሲሆን፡ ከፍ ሲል ደግሞ በኢትዮጽያዊነቱ የሚኮራ ነበር። አሁንም ቢሆን፡ አውራጃዊ ስሜት ትግራይከሚለው ስሜት ያይላል። በኤርትራም እንደዚያው ነው። የትግራይ እና የኤርትራ ዘመናዮⶭ ከፈረንጆⶭ የሰነቁትን የጥላⶭ ፍሬ፡ ከበረሃ ምሽጋⶨው ሆነው እየዘሩኤርትራንና ትግራይ አሚለውን ማንነት ለመፍጠር ብዙ ተጉዘዋል። በዚ አንጻር ሲታይ፡ የመሃል አገር ሰው አውራጃነትን ከተወ ዘመናት አልፈዋል። አነሰ ቢባልበጎንደር፡ጎጃም፡ወሎ እና ሽዋ ነው እሚያስበው፡ ያም ቢሆን በጣም የደበዘዘ ነው። አብዛኛው የነዚህ ጠቅላይ ግዛቶⶭ ህዝብ በኢትዮጽያዊነቱ ይቆረቆራል። ይሄከፍተኛ የእድገት ልዩነት ነው። ለዚህም ነበር፡ ወራሪዎⶭ፡ ይህንን የኢትዮጽያ ክፍልንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለይተው ሲዘምቱባⶨው የነበረውና፡ አሁንምበተወካዮⶫⶨው በኩል ያንን የሚያደርጉት። ትምክህተኛ እያሉ የሚጠሩት፡ ከነሱ ልቆ ስለሄደ ነው። እነሱ በአውራጃ በሚያስቡበት ጊዜ፡ የጠቀስኩዋⶨው የመሃልአገር ሰዎⶭ ኢትዮጽያዊነትን ያራምዱ ነበር። ትምክህቱ እንግዲህ ላቅ ብለው ማሰባⶨው ነው።በህብረተሰብ እድገት ደረጃ -ቤተሰብ፡ዘመድ፡ መንደር፡ወረዳ…ወዘተ…- እያልን በምንመዝንበት ጊዜ፡ ላቅ ብሎ እምናገኘው ኢትዮጽያዊ የመሃል አገሩ ነው። ለዛም ነው፡ በኢትዮጽያዊነቱ እማያመነታው።


ጣልያን፡ ኤርትራን ሲለቅ፡ ኤርትራዊነት የሚለውን ስሜት ለመፍጠር ቢሞክርም፡ ቢዙም ሳይሳካለት ነው አገሩን ለቆ የሄደው። የኤርትራን የማንነት ስሜትመፍጠር ያልቻለው ጣልያን፡ ትግራይ የሚለውንም መፍጠር አልቻለም፡ አንዳንድ የሰሜን ባላባቶⶭን ከማማለሉ በስተቀር። ጣልያንን ተከትሎ የመጣውእንግሊዝ ግን የዋዛ አልነበረምና፡ በደንብ ነው የሰራበት። ከዓድዋ በፕሮተስታንት እምነታⶨው ምክንያት በድንጋይ ተወግረው የተባረሩት አቶ ወልደማርያም፡ ወደኤርትራ ሄዱና ከአንድ የሰራየ ሴት ወልደአብ የሚባል ልጅ ወለዱ፡ ብሁዋላ አቶ ወለደአብ ወልደማርያም የተባሉት፡ፕሮቶስታንቱ፡ የኤርትራው ብሄረተኛመሆናⶨው ነው። ያኔ ነው፡ በእንግሊዝ መንግስት የትግራይ ትግርኚ የሚለውን ሃገር የመከፋፈል ደባ፡ ከኦጋዴን ፕሮጀክቱ ጋር አዳብሎ የገፋበት። ይሄ እንግዲህበ1930ዎⶩ (በአውሮጻውያኑ 1940ዎⶩ)መሆኑ ነው። በዛን ጊዜ በኤርትራ የተወለዱ ሰዎⶭ አሁን የ80 ዓመት እድሜ ባለጸጎⶭ ናⶨው። እነዚህ ናⶨውእንግዲህ፡ ያ በልጅነታⶭው የተለከፉበት መርዝ አለቅ ብሎአⶨው ለሺዎⶭ አመታት አንድ ሆኖ የኖረውን ህዝብ በዘረኝነት ሲያተራምሱት እሚታዩት። ለነገሩ፡ክአድዋ የሚወለዱት የስብሃት ነጋ ዘመዶⶭ ትውልዳⶨው ከእንግሊዝ ይመዘዛል። 5 ትውልድም አይደርስም፡ ዋአሮ የወለደⶫⶨው ፡የአገር ጎብኚው ማንስፊልድልጆⶭ ናⶨው። ለገሰ ዜናዊ የአበባው የልጅ ልጅ ነው፡ ጎጃሜ። አበባው-ነጋድራስ ተሰማ – አስረስ- ዜናዊ:፤ ይገርማል! መለስ ዘሩ ጠፋበትና፡ ወንድም ከወንድምሲያጋድል ሴኦል ገባ። ወይ ጉድ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials