ቱርክ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን ተከትሎ ተጨማሪ 1 ሺህ 389 ወታደሮች አገደች
የቱርክ መንግስት በቅርቡ የከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ውስጥ እጃቸው አለ ያላቸውን ወገኖች ከስራ እያባረረ ይገኛል።
የገሀሪቱ መንግስት ከስራ እያገዳቸው ካሉት ሰዎች ውስጥ ደግሞ የሀገሪቱ ጦር አባላት ይገኙበታል።
ዛሬ በተሰማው መረጃም የቱርክ መንግድት ከ15 ቀን በፊት በተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ውስጥ እጃቸው አለበት ያላቸውን 1 ሺህ 389 የጦር አባላት ከስራ አግዷል።
የዛሬውን ጨምሮ እስካሁን ከስራ የታገዱት የሀገሪቱ የጦር አባላት ቁጥርም ከ3 ሺህ በላይ መድረሱ ነው የተነገረው።
የቱርክ መንግስት ከከሸፈው የመፈንቅለ መግንስት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን በርካታ መምህራን፣ ጋዜጠኞች፣ ወታደሮች እና የመንግስት ሰራተኞች ከስራ ማገዱ ይታወሳል።
ከመፈንቅለ መንግስት ሙከራው ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውም ይታወሳል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
No comments:
Post a Comment