Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, August 7, 2016

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በንጹሃን ሰልፈኞች ላይ መንግስት እየፈጸመውን የሚገኘውን ግፍ ለማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ወሰኑ።



ኢትዮጵያውያን  በጀርመን ኑረምበርግ በምትባል ከተማ ነሃሴ 1 2008 ዓም ባደረጉት ታላቅ ስብሰባ በመላው  የኢትዮጵያ ክፍል እየተቀጣጠለ ባለው የሀዝብ ለአምባገነናዊ  ስርአት አልገዛ ባይነት ምክንያት በመንግስት ታጣቂዎች  እየተፈጸመ  ያለውን ግድያ እስራት እንዲሁም ድብደባ አውግዘዋል። በተጨማሪም  በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ  ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ  ሁኔታ  በንጹሃን  ኦሮሞ እና አማራ ህዝብ የመንግስት ታጣቂዎች እየፈጸሙ ላሉት የነፍስ መገደል እና እስራት በመቃወም  በጀርመን በርሊን ከተማ  ድምጻቸውን ለአለም ለማሰማት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት ፕሮግራም  አዘጋጅተዋል።ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

በስብሰባውም  የአርበኞች ግንቦት ሰባት የኮምኒኬሽን  ሀላፊ አርበኛ ኑር ጀባ ከኤርትራ ቀጥታ  በስልክ መስመር በመግባት ለታዳሚው  ከእያንዳዱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚነሱት ህዝባዊ አመጽ ጀርባ  የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ እንቅስቃሴ አለበት በማለት ማረጋገጫ  ሰጥቶል። የኮምኒኬሽን  ሀላፊው አርበኛ ኑር ጀባ በማከልም አምባገነናዊነትን ዘረኝነትን እንዲሁም ኢፍትሃዊነትን በመቃወም  በአደባባይ በመንግስት ሀይሎች በጥይት ለረገፉት ንጹሃን የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች የወያኔ መንግስት ሃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ መውሰድ እንዳለበት አሳስቧል። እንደ አርበኛ  ኑር ጀባ  ገለጻ መሰረት አርበኞች ግንቦት ሰባት የወያኔን መንግስት በ3 ዓይነት መንገድ እየታገለ መሆኑን ለታዳሚው  ገልጸዏል። 1ኛው ህዝባዊ አመጽ በአገር ውስጥ በማነሳሳትና በመደገፍ 2ኛው ከኢትዮጵያ ውጭ  ወያኔንና የወያኔ ድርጅቶችን የማዳከም እንቅስቃሴ 3ኛው የትጥቅ ትግል ናቸው።  በተለያዩ  ጊዜያት የወያኔን ስርዓት በሀይል ለመጣል በሚደረገው  የትጥቅ ትግል በውጭ  የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት የሚገኘውን  የሞራል የቁሳቁስ የገንዘብ እርዳታ አርበኛ ኑር ጀባ  በሰራዊቱ ስም  ታላቅ ምስጋናውን በማስተላለፍ ፤ ይሀ ዓይነቱ  ድጋፍ  በሰፊው  እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፉዋል። ታዳሚውም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች
የሚገኘው  የኢትዮጵያ ህዝብ በጨቋኞች አምባገነኖችና ከፋፋዮች መገዛት በቃኝ ብሎ  በአደባባይ ጸረ ወያኔ ትግሉን ለወራት አፏፉሞ በመቀጠሉ እና እጅግ አስገራሚ መስዋቶችን እየከፈለ በመሆኑ ለዚህ  ትግልን የተፈለገውን ግብ እንዲመታ  ለመደገፍ ወስነዋል። በዚህ የአቁዋም መግለጫ በውጭ አገር የሚኖሩ መላው ኢትዮጵያውያን በንጹሀን ህዝቦች ላይ ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ እና ግድያ ሲፈጸም ቸል ማለት እንደሌለበት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ይህንን ተከትሎም  ታዳሚው ለኢትዮጳያ ህዝብ  ያለውን አጋርነት ከዚሀ በታች በተዘረዘሩት እንቅስቃሲዎች ገልጸዋል።
1ኛ የወያኔ ኢህአዲግ በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ በማጋለጥ
2ኛ በበርሊን ከተማ  ከፍተኛ የተቁዋሞ ሰልፍ በማዘጋጀት የአለም  አቀፍ ማህበረሰብ በወያኔ ላይ ተጽእኖ እንዲያደርግ በመታገል
3ኛ አለአግባብ  የታሰሩ የህዝብ ተወካዮች ጋዜጠኞች የፖለቲካና የሀይማኖት መሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ
4ኛ ወያኔ ኢህአዲግ ሃገሩንና ህዝቡን ማስተዳደር ስላልቻለ በአስቸኩዋይ  ከስልጣን የሚወርድበትን እንዲሁም ስልጣኑን ለህዝብ አስረክቦ የሽግግር መንግስት ለመመስረት  የሚያስችል ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ  እንዲካሄድ መንገዶች በመፍጠርና በማመቻቸት ናቸው።

ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

No comments:

Post a Comment

wanted officials