Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 26, 2016

ስንታየሁ ቸኮል ያለበት ሊታወቅ አልቻለም!







ነሐሴ 16 ቀን 2008 ዓ.ም አራዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርቦ በዋስ እንዲወጣ ብይን የተሰጠው ስንታየሁ ቸኮል፣ ከእስር ካለመለቀቁ በተጨማሪ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ያለበት ቦታ ሊታወቅ አልቻለም። በትላንትናው ዕለት የአራዳ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ስብሃት ገ/መድህን ከእስር ሊለቀቅ ያልቻለበትን ምክንያት በማስመልከት ላነሳልናቸው ጥያቄ “ሌላ የሚፈልገው አካል ስላለ ልንለቀው አንችልም!” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው ይታወቃል። የሚፈልገውን አካል ማንነት ከመናገር የተቆጠቡት ኃላፊው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስንታየሁን ማዘዋወራቸውን በዛሬው ዕለት ገልፀውልናል። ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመሄድ ስንታየሁ፣ ወደዛ መዘዋወሩን ለማጣራት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የዕለት ሁኔታ ኃላፊ የሆኑት ሳጅን ለምለም አደምን፣ ያነጋገርን ሲሆን ስንታየሁ ቸኮል የተባለ እስረኛ ወደእነሱ አለመዘዋወሩን ገልፀው ወደ አረዳ ፖሊስ መምሪያ ሄደን እንድንጠይቅ ነግረውናል። ሁለቱም አካል እኛ ጋር የለም ማለታቸውን ተከትሎ ወደፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) በማቅናት ወደዛ መዘዋወሩን ብንጠይቅም “እንደዚህ የሚባል እስረኛ አልተዘዋወረም!” የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል። (እዮኤል ዳምጤ)

No comments:

Post a Comment

wanted officials