Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 12, 2016

በባሕር ዳር የዐማራ ፖሊስ በንዴት አምስት ፌደራሎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ








በባሕር ዳር የዐማራ ፖሊስ በንዴት አምስት ፌደራሎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ


• (የገዱ አንዳርጋቸው መነሳት የዐማራን ተጋድሎ ወደፊት ያስፈነጥረዋል!!)
• የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የነበረው ድርድር ያለስምምነት ተበትኗል
• በባሕር ዳር የዐማራ ፖሊስ በንዴት አምስት ፌደራሎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ
• ‹‹አታልቅሱ፤ ልጄ ለተቀደሰ ዓላማ ተሰውቷል›› በባሕር ዳር ልጃቸውን ያጡ እናት
• ወረታ ከተማ የመጠጥ ውኃ ውስጥ መርዝ ሊጨምር የነበረው ግለሰብ እብድ ነኝ በማለት እያጭበረበረ ነው የዐማራ ተጋድሎ የነሃሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም (ከኹመራ እስከ ሸበል በረንታ) ዘገባ


Muluken Tesfaw - ኹመራ፤ በአሸባሪነት ስም የማንነት ጥያቄያቸውን ሊያደፋፍኑት ቢጥሩም እንደማይሳከ የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች ተናግረዋል፤
ዛሬ በኹመራ፣ በዳንሻና በአዲረመጥ ከተማ ያነጋገርናቸው የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች እንደሚናገሩት የማንነት ጥያቄያችን ለማዳፈን የአሸባሪነት ስም እየሰጡ በየሰአቱ ይፈትሹናል፡፡ አማርኛ የሚናገር ሰው ሁሉ እንዲሸማቀቅ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከኹመራ ያገኘነው ግለሰብ ‹‹አሁን የማወራህ ከፎቅ ላይ ወጥቼ ነው፤ በየቦታው እኛን የሚከታተል የትግራይ ሰው በየቦታው ነው፡፡ ያለንበትም ሁኔታ ያስጠላል›› ሲል የሚደርስበትን ጫና ገልጧል፡፡
የወያኔ ሰዎች አንዳንድ ዐማሮችን በገንዘብ በመግዛት መሣሪያ አስታጥቀው ወደ በርሃ በመላክ ከተወሰ ቀን በኋላ ‹‹ምሕረት ጠይቀናል›› ብለው ይመለሳሉ፡፡ በኋላም የወልቃይት ጠገዴ ዐማሮች እንዳስታጠቋው በመግለጽ ድራማ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡ በዚሁ አያይዘውም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንና የተቃዋሚ ድርጅቶች የወልቃይት ጠገዴን ዐማራ የማንነት ጥያቄ ዘገባ ሲሠሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብሎም በእውነት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
አርማጭሆ፤ በታችና በምዕራብ የአርማጭሆ እንዲሁም በጠገዴ አካባቢዎች ውጥረት እንዳለ ከቅራቅር ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሦስት ቀናት ኩርቢ አካባቢ ከ30 በላይ የመከላከያ ሠራዊትና ሦስት መኪኖች ሙሉ በሙሉ በሕዝቡ መደምሰሳቸው ታውቋል፡፡ ከሦስት መኪና ውስጥ ከነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ውስጥ ቁጥራቸው አምስት የሚሆኑ ብቻ በከፍተኛ ቁስል መትረፋቸው ነው የተነገረው፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ የቅራቅር ከተማ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ትናንት ደግሞ ‹‹ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን ካስፈለገ የአርማጭሆ ሕዝብ መሣሪያ ማውረድ አለበት›› በማለት ስብሰባ ላይ የተናገረ የሕወሓት ካድሬ በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃጂራ ከተማ ተገድሏል፡፡

ጎንደር፤ በከፍተኛ ባለሥልጣናት የተካሔደው ስብሰባ ያለ ምንም ውጤት ተበትኗል
በጎንደር ዛሬ ነሐሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. በአቶ አዲሱ ለገሠ እና በአቶ በረከት ስምዖን የተመራው የከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብሰባ ያለ ምንም ውጤት ተበትኗል፡፡ የጎንደር ከተማ እና የሰሜን ጎንደር ዞን የካቢኔ አባላት ‹‹ከዚህ በኋላ ከሕዝባችን ጎን እንቆማለን›› ብለው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ በስብሰባው የተነሱ አጀንዳዎች ‹‹የተገደሉ ሰዎችን ኃላፊነት አገዛዙ ይውሰድ፤ የወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈታ›› የሚሉ ሲሆኑ ከፍተኛዎች ባለሥልጣኖች ከሕወሓት በኩል የተሰጣቸውን ተልእኮ ለማስፈጸም ሙሉ በሙሉ ቢንቀሳቀሱም ተሳታፊዎች ትተዋቸው ወጥተዋል፡፡ በሽምግልና ለመፍታት የተደረገው ሴራም አልተሳካም፡፡ የካቢኔ አባላቱ ስብሰባውን ረግጠው ሲወጡ ችግር ይፈጠራል ተብሎ ቢሰጋም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት ነገር እንዳልነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሕዝቡ የእለት ተለት እንቅስቃሴም የተገደበ እንደሆነ ከቦታው የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ነገ ነሐሴ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በጎንደር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን በአውሮፕላን የማስወጣት ሥራ እስከዛሬም ድረስ እየተከናወነ እንደሆነ ተገልጧል፡፡
ወረታ፤ በወረታ ከተማ የመጠጥ ውኃ ውስጥ መርዝ ሊጨመር ሲል የተያዘው ሰው እብድ ነኝ በማለት ለማታለል እየሞከረ እንደሆነ ዛሬ ከቦታው በስልክ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸውልናል፡፡ ግለሰቡ ትግሬ ከመሆኑም በላይ ብዙም አማርኛ የማይችል ሲሆን የአእምሮ ጤነኝነት እንደሌለው ለማሳየት እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ ‹‹የአእምሮ ጤነኛ ያልሆነ ከሆነ እንዴት በድብቅ ያን ያክል ሰው ጨራሽ የሆነ ኬሚካል ለመጨመር ፈለገ? ምን ሊሠራና ማን ወረታ አመጣው?›› በማለት መገረማቸውን ገልጸዋል፡፡
ከወረታ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ያክል የሚገኙት የአዲስ ዘመንና የይፋግ ከተሞች እሁድ ለት የተጋድሎ ሰልፍ ከወጡ ወዲህ እስካሁን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደሌለ ነው የተገለጸው፡፡ በአዲስ ዘመንና በይፋግ በተጋድሎ የተሰው ሰዎች ብዛት ሦስት ነው ተብሏል፡፡
ደብረ ታቦር/ ነፋስ መውጫ፤ በደብረ ታቦር አንድ የኦሮሞን ሾፌር ሕዝቡ ጥበቃ አድርጎ ሸኝቶታል
በደብረ ታቦርና ነፋስ መውጫ ከተሞች እስካሁን ድረስ ውጥረት እንዳለ ነው፡፡ አንዳንድ ቅጥረኞች የተጋድሎ መሪ ናቸው ያሏውን ሰዎች በሌሊት እያሳፈኑ መሆኑን የታወቀ ሲሆን እነዚህ ግለሰቦች በቤተሰቦቻቸው እንዲመከሩ ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከነፋስ መውጫ ትንሽ ራቅ ብላ ባለችው የጨጭሆ መንደር ያሉ ዐማሮች እስካሁን ድረስ ተጋድሏቸውን አላቆሙም፡፡
በደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ለት በነበረው ተጋድሎ አንድ የተሳቢ መኪና የያዘ ሰው በተጋድሎው መካከል ሲመጣ ሕዝቡ መኪናውን ሊያወድም ሲል ‹‹እባካችሁ እኔ እንደናንተ የተገፋሁ ወገን ነኝ እንጅ ወያኔ አይደለሁም›› በማለት መታወቂያውን ሲያሳይ የኦሮሞ ተወላጅ ሆኖ ተገኘ፡፡ በዚህም ሕዝቡ ‹‹አንተማ የእኛው ወንድም ነህ›› በማለት ከሎሚ ዱር እስከ መሎ ድረስ ሰው ተመድቦ በሰላም እንዲሸኝ ተደርጓል፡፡
ባሕር ዳር፤ የባሕር ዳር ዐማሮች እስካሁን ትግል ላይ ናቸው፡፡ እሁድ በነበረው ተጋድሎ የዐማራ ክልል ፖሊሶች ከዱላ በቀር ምንም ዓይነት መሣሪያ እንዲይዙ አልተፈቀደላቸውም ነበር፡፡ የወያኔ ወታደሮችንና የፌደራል ፖሊሶች በዐማሮች ላይ የሚያደርጉትን ጭፍጨፋ የተመለከተ የዐማራ ክልል ፖሊስ ትናንት በንዴት አምስቱን የፌደራል ፖሊሶች ካጋደመ በኋላ ራሱን ማጥፋቱን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህ ጀግና ለሌሎች የክልሉ ፖሊሶች ያሳየው አርአያነትን የሚያደንቁት የባሕር ዳር ወጣቶች ‹‹ራሱን ባያጠፋ ኖሮ በምንም መልኩ አሳልፈን አንሰጠውም ነበር›› ሲሉ በቁጭት ገልጸዋል፡፡
በጎጃም ሌላም የሰማነው አስገራሚ ታሪክ አለ፤ እሁድ በነበረው ተጋድሎ ልጃቸው የተሰዋባቸው እናት ለሀዘን የሚሔዱትን ዐማሮች ‹‹አታልቅሱ! የእኔ ልጅ የተሰዋው ለተቀደሰ ዓላማ ነው!! አባቶቻችን ለሕዝባቸውና ለአገራቸው ያደረጉትን መስዋትነት ስለከፈለ ደስተኛ ነኝ›› በማለት ሀዘንተኞችን ሲያጽናኑ በቦታው የነበሩ ዐማሮች በንዴትና በሚታያቸው ተስፋ የበለጠ ያነቡ እንደነበር የመረጃ ምንጫችን ከባሕር ዳር ተናግሯል፡፡
ባሕር ዳር ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ የማይታይባት ከተማ እንደሆነች የተናገሩት የመረጃ ምንጮቻችን በጢስ ዓባይና በዘጌ በኩል ያሉ ገበሬዎች ከመከላከያ በሚደርስባቸው ጥቃት ልክ አጸፋ እየሰጡ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ በባሕር ዳር የሞቱት ሰዎች ከ70 በላይ ደርሷል፡፡ አንድ የዐይን ምስክር ‹‹ከ12 በላይ አስከሬን ሲነሳ ተመልክቻለሁ›› ብሏል፡፡
ደብረ ማርቆስ፤ ደብረ ማርቆስ ከተማ ቀጣይ ቅዳሜ የተጋድሎ ሰለፍ ለማካሔድ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ የደብረ ማርቆስ ዐማሮች በቀጣይ ቅዳሜ በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ ይወጣሉ፡፡
ሸበል በረንታ፤ የሸበል በረንታ ጀግኖች በወረዳው የነበረውን የጥይት መካዘን ተከፋፍለዋል፡፡ እሁድ ለት ለተጋድሎ የወጡት የሸበል በረንታ ዐማሮች በወረዳው አስተዳደር (ፖሊስ) ጽ/ቤት የነበረውን የመሣሪያ መካዘን ውስጥ የነበረውን የተለያየ መሣሪያ ዐማሮች ተከፋፍለዋል፡፡
የዐማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials