Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 19, 2016

ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ካናዳ፣ አውሮፕላ እንዲሁም አፍሪካ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ግድያና እስር በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የሚደረገውን ግድያና እስር በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ
ኢሳት (ነሃሴ 9 ፥ 2008)
ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ካናዳ፣ አውሮፕላ እንዲሁም አፍሪካ የሆኑ ኢትዮጵያውያን መንግስት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በንጹሃን ሰዎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያና የጅምላ እስራት በመቃወም በሳምንቱ መገባደጃ ሰላማዊ ሰልፎችን አካሄዱ።
በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማና አካባቢው የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ህዝቡ ያቀረበውን ሰላማዊ ጥያቄ ህጋዊ ምላሽን እንዲያገኝ ጠይቀዋል።
ሰላማዊ ጥያቄን እያቀረቡ ካሉ ዜጎች ጎን መቆማቸውን ሲገልጹ ያረፈዱት ሰልፈኞቹ በመግንስት የጸጥታ ሃይሎች እየተወሰደ ያለው ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆምና መንግስት ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ አስታውቀዋል።
ነዋሪነታቸው በአውሮፓዊቷ አገር ስዊድን መዲና ስቶኮልም ከተማ የሆነ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ መልኩ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍን በማካሄድ በተለያዩ የኦሮሚያና አማራ ክልሎች በሚገኙ ከተሞች በመፈጸም ላይ ያለን ግድያ አውግዘዋል።
በሳምንቱ መገባደጃ እሁድ በካናዳ ኤድመንተን ከተማ እንድሁም በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ የምገኙ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ መልኩ የተቃውሞ ዝግጅቶችን እንዳካሄዱ ከየከተሞቹ ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመልክቷል።
በካናዳዋ ኤድመንተን ከተካሂደው የተቃውሞ ዝግጅት በተጨማሪ፣ ከካልጋሪ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ ዝግጅት ሰሞኑን እንዳካሄዱ ተባባሪ ባልደርባችን ጸጋዬ ቦሬ ከስፍራው ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በዚሁ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን በመቃወም ነዋሪነታቸው በብሪታኒያ ለንደን ከተማ እንዲሁም በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ ሰኞች እንደተካሄደ አዘጋጆች ለኢሳት አስታውቀዋል።
በሁለቱ ከተሞች የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን መንግስት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈጸመውንና እየፈጸመ ያለውን ግድያ በመቃወም ድርጊቱን እንደሚያወግዙ የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዳቀረቡ ታውቋል።
በሁለቱ ክልሎች እየተፈጸመ ያለው ግድያ ተከትሎ ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ የሚናፖሊስ ግዛት ሚኔሶታ ከተማ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የተቃውሞ ትዕይንቶች መካሄዳቸው ይታወሳል።
ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሁለቱ ክልሎች በተፈጸሙ የጸጥታ ሃይሎች እርምጃ ከ100 የሚበልጡ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ለወራት በኦሮሚያ ክልል በሰነበተው ተቃውሞ ከ400 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን አለም አቀፍ ተቋማት ይገልጻሉ።


 

No comments:

Post a Comment

wanted officials