Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 9, 2016

በባህርዳር የጢስ አባይ ነዋሪዎች እና ወታደሮች ሲታኮሱ ዋሉ






ነሃሴ ፫ ( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ የተገደለውን አንድ የጢስ አባይ ተወላጅ ደም ለመበቀል የሟች ቤተዘመዶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ሌሊቱን ከአጋዚ ጦር ጋር ጠበንጃ አንስተው ሲዋጉ ማደራቸው ከጢስ አባይ የወጡ መረጃዎች የክልዩ ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡በጢስ አባይ ከተማ ያለው ውጥረት እየተባባሰ በመሄዱ ዛሬ ረፋዱ ላይ ከአንድ መቶ ሃያ በላይ ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት ከተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች በአንቶኖቭ በመምጣት ወደ ጪስ አባይ ለውጊያ ተልኳል፡፡ የአካባቢው ታጣቂም ፍልሚያውን አጠናክረው ቀጥለዋል።


ጢስ አባይ ከባህርዳር በቅርብ እርቀት ላይ የምትገኝ የአባይ ፏፏቴ የሚገኝባት መለስተኛ ከተማ ናት።

በተመሳሳይ ዜና የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ወደ ሰሜን ጎንደር ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በመጓዝ ህዝቡ ተቃውሞ እንዳያነሳ በሃይማኖት አባቶች በኩል ለማስገዘት እና አመራሩን እና ህዝቡን ለማስታረቅ ያደረጉት ሙከራ በአብዛኛው ሳይሳካ ቀርቷል።

በጎንደር ሲኒማ አዳራሽ የአብዴኑ በረከት ስምኦን የኢህአዴግ ደጋፊዎችን ብቻ በመጥራት ስብሰባ ለማድረግ መሞከሩ ሲሰማ ወጣቱ በብዛት ወደ አዳራሹ በመግባቱና ጠንካራ ጥያቄዎችን መጠየቅ በመጀመሩ፣ አቶ በረከት በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነን ስብሰባ ለማድረግ ስለማንችል ስብሰባው ተበትኗል ብሎ ስብሰባው እንዲበተን ካደረገ በሁዋላ፣ ወጣቶቹ በቁጣ አዳራሹን በድንጋይ የደበደቡ ሲሆን፣ አቶ በረከትም በወታደሮች ታጅቦ ወጥቷል። ወጣቱ ተቃውሞውን በሚቀጥልበት ወቅት በከተማው በብዛት የሚገኙት ወታደሮች አስለቃሽ ጭስ በመበተን ለመቆጣጠር ሙከራ አድርገዋል።

ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ ነገ ረቡዕ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ትበሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የጎንደር ነዋሪዎችም በቦታው ተግኝተው ተቃውሞ እንደሚያሰሙ እየተናገሩ ነው።

በሳንጃ ከተማ ደግሞ የብአዴን ባለስልጣናት የሃይማኖት አባቶችን በመያዝ የስርዓቱን ወታደሮች እና አርሶደሮችን ለማስታረቅ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን፣ አርሶአደሮች ወታደሩ ድንበር መጠበቅ ሲገባው የገዛ ህዝቡን እንዴት ይጨፈጭፋል በማለት በቁጣ ሲናገሩ ውለዋል።

በተለያዩ የአማራ ከተሞች በሳምንቱ መጨረሻ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች የተጀመሩ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ በርካታ የመከላከያ ሰራዊቱን በየከተሞች እየወሰደ በማስፈር ላይ ነው። የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው ወጣቶች ወታደሮችን ከምንም ባለመቁጠር በሰልፉ ላይ ለመገኘት ዝግጀቶችን እያደረጉ ነው። ተቃውሞውን ሊመሩ ይችላሉ የተባሉ ወጣቶች እየተመረጡ በመታሰር ላይ መሆናቸውም ታውቋል።

በኦሮምያ ክልል ደግሞ ፖሊሶች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ላገለገሉበት የ ስራ የውሎ አበል በሚል እስከ 500 ብር በነፍስ ወከፍ ተከፍሎአቸዋል። የአዲስ አበባ ፖሊሶች በተቀራኒው ወደ ባህርዳር ሄደው ስራ እንዲሰሩ ሲጠየቁ፣ ደሞዝ የጨመራችሁለት አካል ይሂድ እኛ አንሄድም ብለው መቃወማቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ፖሊሶች አድማ የመበተን ልምድ አላቸው በሚል ወደ ባህርዳር ሂደው በከተማው የተነሳውን ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲያበርዱ በገዢው ፓርቲ በኩል ፍላጎት እንደነበር ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials