Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 10, 2016

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየተፈጸመ ያለን ግድያ በመቃወም ሰልፍ አደረጉ



ኢሳት (ነሃሴ 3 ፥ 2008)ዲሲ


ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማና አካባቢዋ የሆነ ኢትዮጵያውያን በኦሮሚያ አማራ ክልሎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየተፈጸመ ያለን ግድያ በመቃወም ማክሰኞ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።


እየተፈጸመ ያለውን ግድያና እስራት እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ጥያቄን ሲያቀርቡ ያረፈዱት ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ መንግስት ከአምባገነን መንግስታት የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆም አሳስበዋል።


የአሜሪካ መንግስት በየአመቱ በኢትዮጵያ ስለሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርትን ቢያወጣም የወሰደው እርምጃ የለም በማለት ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያላቸውን ቅሬታ አቅርበዋል።


“ግድያ ይብቃ” “የዜጎች መብት ይከበር” “ወልቃይት ጎንደር ነው” የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ የነበሩት ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ መንግስት ህጻናትና ሴት እናቶችን የሚገድል መንግስት ከመደገፍ እንዲታቀብ ጠይቀዋል።


No comments:

Post a Comment

wanted officials