
ከታምራት ሲሳይ
1. ሉዋንዳ
የአንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ በአፍሪካ በነዳጅ ምርት፣ የባህር ወደብና የአስተዳደር ማዕከል ናት:: በአለፉት አስርት ዓመታት ከአፍሪካ አገራት የላቀ ዕድገት አሳይታለች::
በቻይና የኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን ግንባታ እንደ ምዕራባዊያን ከተሞች የመጠቀች ሆናለች::

2. አጋዲር
የሞሮኮ አንዷና ዋነኛ ከተማ ናት:: ከተማዋ በ1960 በርዕደ መሬት ከተመታች በኋላ እንደገና የተገነባች ናት:: አሁን የባህር ዳርቻ ያላት የጎብኝዎችን ቀልብ ከመላው ዓለም የምትስብ ተመራጭ ከተማ ከሥራ ቦታ በሚጠፉ ሰራተኞች የተዘጋው ሆናለች::

3. ናይሮቢ
የኬኒያ መዲና እና ትልቋ ከተማ ናት። ከምስራቅ አፍሪካ ከተሞች በህዝብ ብዛትም ቀዳሚ ናት:: ከአፍሪካ በፖለቲካም ሆነ በምጣኔ ሀብት ዕድገት ከመሪ ከተሞች ተርታ ተሰልፋለች:: የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚበዙባትና ዓለማቀፍ ተቋማት የከተሙባት በመሆኑ ደማቅ አድርጓታል።

4. ሌጐስ
በህዝብ ብዛቷ ከናይጀሪያ ቀዳሚ የአገሪቱ መዲናም ናት:: የሌጐስ ደሴት ከሰማይ ጠቀስ ፎቆችዋና በጅምላ ንግድ ማዕከልነቷ ትታወቃለች:: ከበርካታ ብሔሮቿ ውበት ጋር ተዳምሮ ከተማዋ ውብና ደማቅ መሆን አስችሏታል።

5. ካይሮ
የስልጣኔ መናኸሪያዋ፣ የግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ከመካከለኛው ምስራቅ አገራት እና ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቋ ከተማ ናት:: ከተማዋ የ24 ሰዓት ከተማ ተብላም ትታወቃለች:: ካይሮ 24 ሰዓት ሙሉ ደምቃ ውላ ታነጋዋለች።
No comments:
Post a Comment