Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, August 18, 2016

ወረታ ከተማ በአሁኑ ሰአት ምድር ቀውጢ ሆናለች





ነሐሴ 22/2008 ዓም ከባህርዳር አካባቢ ተነስቶ በሀሙሲት አድርጎ በደብረታቦር አድርጎ ወደ መቀሌ በመጓዝ ላይ የነበረ ወታደሮችን የጫነ ኦራል ጉመራ ወንዝ ላይ በጀግኖቹ የጎንደር ወጣቶች ጉመራ ወንዝ ላይ ድልድዩን በመዘርጋታቸው መሻገር ባለመቻሉ መሄጃ ያጣው ሠራዊት ወደ ጎንደር ለመመለስ ተገዷል ከጉማራ ሸሽቶ ወደ ጎንደር ሲሮጥ ሌሎቹ ጀግኖች ርብ ወንዝን በመዘርጋት መውጫ ቀዳዳ አሳጥተው እየተንከራተተ እንደሚገኝ ታውቋል.

ወረታ ዘግየት ብላ ህዝባዊ እንቢተኝነቱን እያካሄደች ነው ወረታ ከተማ በአሁኑ ሰአት ምድር ቀውጢ ሆናለች የወረታ ህዝብ ምድር አንቀጥቅጥ ተቃውሞ እያካሄደ ነው!


#ደብረታቦር

በደብረታቦር፣ በወረታ እና በአዲሥ ዘመን ከተሞች ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀን የስራ ማቆም አድማው የተጀመረ ሲሆን ደብረታቦር ከተማ በዚህ መልኩ ፀጥ ረጭ ብላለች።

No comments:

Post a Comment

wanted officials