Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 26, 2016

በአዲስ አበባና በጎንደር ጉዟቸውን ሲጠባበቁ የነበሩ 9ሺ ቤተ-እስራዔላውያን ወደ እስራዔል ሊጓዙ ነው


ኢሳት (ነሃሴ 17 ፥ 2008)
የእስራዔል መንግስት በቅርቡ እንዲዘገይ ያደረገውን እና ተቃውሞ አስነስቶ የነበረውን የዘጠኝ ሺ ቤተ-እስራዔላውያንን ጉዞ ከሶስት ወር በኋላ እንደሚጀምር ይፋ አደረገ።
በጎንደር እና አዲስ አበባ ከተሞች ለአመታት ጉዟቸውን በመጠበባቅ ላይ የንበርሩ ቤተ እስራዔላውያን በፊታችን ህዳር ወር ጀምሮ ወደ እስራዔል መግባት እንደሚጀምሩ የሃገሪቱ የቤተ እስራዔላውያን ኤጀንሲ መግለጹን ታይምስ ኦፍ እስራዔል የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል።
የእስራዔል የፋይናንስ ሚኒስቴር ወደ ዘጠኝ ሺ አካባቢ የሚጠጉትን ቤተ እስራዔላውያንን ለማጓጓዝ በጀትን ያጸደቀ ሲሆን፣ ከወራት በፊት በበጀት እጥረት በሚል ጉዞው እንዲዘገይ መደረጉ ይታወሳል።
ይሁንና፣ የሃገሪቱ መንግስት ያስተላለፈውን ይህንኑ ውሳኔ ተከትሎ በእስራዔላውያን የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱ ከበጀት ችግር ጋር የተያያዘ ሳይሆን፣ በሃገሪቱ እየተስፋፋ ከመጣው የዘረኝነት ጉዳይ ጋር የተገናኘ ነው በማለት ተቃውሞ ሲያካሄዱ ቆይተዋል።
ከኢትዮጵያውያኑ የቀረበውን ተቃውሞ ተከትሎ የእስራዔል ባለስልጣናት ጉዳዩን ዳግም በማጤን ቤተ እስራዔላውያን እንዲያጓጉዙ ውሳኔ ማስተላለፋቸው ታውቋል።
ከመጪው ህዳር ወር ጀምሮ በየወሩ 100 የሚሆኑ ተጓዦች ወደ እስራዔል ይጓዛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የጉዞ ሰነዳቸው ያለቀላቸው 90 ቤተ-እስራዔላውያን በቅርቡ ወደ ሃገሪቱ እንደሚገቡ ባለስልጣናት ለእስራዔል መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው የነበሩት የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሃገራቸው በጎንደር እና አዲስ አበባ ከተማ ለጉዞ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ቤተእስርዔላውያን በቀጣዮቹ አምስት አመታት ውስጥ እንደምታጓጉዝ ይፋ አድርገው እንደነበር የሚታወስ ነው።
የእስራዔል የገንዘብ ሚኒስቴር ወደ ዘጠኝ ሺ አካባቢ የሚሆኑትን ቤተ እስራዔላውያን ወደሃገሪቱ በማጓጓዝና ለማቋቋም ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር አካባቢ እንደሚያስፈልግ በመግለጽ ላይ ናቸው።
ከቤተሰቦቻቸው የተቆራረጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የእስራዔል መንግስት ጉዞው እንዲፋጠን በማድረግ ለአመታት ሲጠበበቁት የነበረው ጉዳይ ዕልባት እንዲያገኝ ጥሪ እያቀረቡ መሆኑም ታውቋል።
በተለያዩ ጊዜያት ወደ እስራዔል የተጓዙ ከ130ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን በሃገሪቱ እንደሚኖሩ መረጃዎች የመለክታሉ።2c159-avereg

No comments:

Post a Comment

wanted officials