Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, August 21, 2016

ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ላሊሳ በሪዮ ኦሎምፒክ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አገኘ – እጁን ወደላይ በማጣመር ለትግሉ ያለውን አጋርነት አሳየ

በሪዮ ኦሎምፒክ በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አገኘች:: ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ላሊሳ በኬኒያዊው አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ ተቀድሞ 2ኛ ቢገባም ውድድሩን በሚያጠናቅቅበት ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ  ባለፈው 10 ወራት ካለማቋረጥ እየተጠቀመበት ያለውን እጅን ወደላይ ማጣመር በማሳየት ለትግሉ ያለውን አጋርነት አሳይቷል::

በዚህ የማራቶን ውድድር አሜሪካዊው ግሌን ሩፕ 3ኛ ሲወጣ ኤርትራዊው አትሌት ግርማይ ገብረስላሴ 4ኛ ሆኖ አጠናቋል::
ኬንያዊው አትሌት ውድድሩን ለመጨረስ 2:08:44 ሲፈጅበት ኢትዮጵያዊው ፈይሳ 2:09:54 ገብቷል:: 3ኛ የወጣው አሜሪካዊው ግሌን 2:10:05 በመግባት 3ኛ ሆኗል::
ፈይሳ ዛሬ በብዙ ሚሊዮኖች በተከታተሉት የኦሎምፒኩ ሜዳ ላይ እጁን ወደላይ አጣምሮ መንግስትን መቃወሙና ከሕዝብ ጎን አጋርነቱን ማሳየቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በሕዝቦች ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያና የሰብ አዊ መብት ጥሰት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት እንዲያደርጉበት የራሱን ጫና ያሳድራል::
 Lalisa

No comments:

Post a Comment

wanted officials