Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 9, 2016

“የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት – እነዚህን 6 ግዴታዎችን እንድትወጣ እጠይቅሃለሁ” – ኮለኔል አለበል አማረ


ጥብቅ ማሳሰቢያ ለአግአዚ ኮ/ክ/ጦር አባላት……..
colenel alebel
በተለይም ለአማራና ለኦሮሞ ተወላጆች ይህንን መልዕክት ለመፃፍ የተገደድኩት ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ /ህወኃት/ የስልጣን ዕድሜውን ለማራዘም ሲል አግአዚን በገዳይነት መጠቀሙን አሁንም በመቀጠሉ ነው። በዚህ በያዝነው ስልጡን አለም ሰውን የሚያክል የተከበረ ፍጡር በየቦታው በፀራራ ፀኃይ በጥይት መግደል እጅግ የሚያሳዝንና ዘግናኝ ነገር ነው። አግአዚ እንደ ክ/ጦር በ1991 ብላቴ ላይ ከመመስረቱ በፊት መለስ ዜናዊ በቅርብ እየተከታትለው በሌ/ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ፣ በብ/ጄኔራል ታደሰ ጋውና፣ በጌታቸው አሰፋ /ያንጊዜ የመለስ ዜናዊ የዘመቻ ጉዳዮች ኃላፊ የነበረ ነው/ እንዲሁም የመለስ ዜናዊ የረጅም ጊዜ የጥበቃ ኃላፊ በነበረው በኮ/ል ነጋሲ ወልዳይና በእኔ ኮ/ል አለበል አማረ ሰፊና ተደጋጋሚ ውይይት በኃላ የተመሰረተ ነው። አመሰራረቱን በጥልቀት ወደ ፊት የምመለስበት ሁኖ፤ በውይይቱ በክ/ጦሩ አመሰራረት ላይ የተለያየ ሃሳብ ተነስተው ነበር በነ ጌታቸው አሰፋና ነጋሲ ወልዳይ በኩል በአነስተኛ የሰው ሃይል ሁኖ ከሶስት ሻለቆች ባልበለጠ እንዲደራጅና ግዳጁም ከመደበኛ ውጊያ ውጭ ሁኖ ጠንከር ያሉ የውጭም የውስጥም ስልጠናወች ተሰጥተውት ዘመናዊ መሳሪያ እንዲታጠቅ የፈለጉ ሲሆን በነፃድቃን በኩል ደግሞ በርከት ያለ የሰው ኃይል እንዲኖረ ትጥቁም ብረት ለበስ ተሽከርካሪወችን ጨምሮ ኤሊኮፕተሮች እንዲኖሩት ግዳጁም መደበኛ ውጊያን ጨምሮ ስፔሻል ግዳጆችንም ግምት ያስገባ እንዲሆን ይፈልጉ ነበር።

በመጨረሻ አደረጃጀቱ የሁለቱንም ፍላጎት በአጣጠመ መልኩ በክ/ጦር ደረጃ ሁኖ እንዲደራጅ ሲደረግ የክ/ጦሩ መሰረት ቀደም ብሎ በ1982 አጽቢ ላይ በህወኃት በኮማንዶ ደረጃ አዲስ አበባ ስንገባ ለVIP ጥበቃ ያስፈልገናል በማለት 180 የሚሆኑ አባላት አሰልጥነው በሁለት ሻለቃ አደራጅተው በኮ/ል ነጋሲ እየተመሩ ቤተ መንግስት ይጠብቁ የነበሩትን እንደመነሻ ወስደን ክ/ጦሩን እንድናደራጅ ተወሰነ። የክ/ጦሩን የሰው ኃይል ለማሟላት የምልመላ መመዘኛ ወጥቶ ከእግረኛ ሰራዊት በርካታ ወታደር ተመልምሎ ወደ ስልጠና እንዲገባ ተደረገ። በዚህ ዝግጅት ላይ እያለንም ኮ/ል ነጋሲ ወልዳይ ሸሸቢት /አዲሃኪም ላይ/ በሻቢያ መድፍ ተመቶ ሞተ። ከነጋሲ ሞት በኃላ ብ/ጄ ገብረኪዳን የሚባል / አሁን የመከላከያ ኢንዶክትሬሽን ኃላፊ/ በአዛዥነት ተመድቦ መጣ። ገብረ ኪዳንም ብዙ ሳይቆይ ሌላ ብ/ጄ ገብረመድን ፈቃዱ የሚባል በም/አዛዥነት ተመድቦ መጣ። ከእግረኛ ተመልምሎ የመጣው ኃይል ስልጠና በኃላ በነበረን በርካታ ሰው ኃይል በብርጌድና በክ/ጦር አደራጀን። በአደረጃጀት ጊዜ መነሻ የነበሩት የህወኃት /ትግሬወች/ ሰወች ሙሉ በሙሉ በየደረጃው አመራርነቱን ያዙት። ከአደረጃጀት በኃል ብ/ጄ ፍስሃ ኪዳኔ በአዛዥነት ተመድቦ መጣ፣ እንዲሁም ብ/ጄ ሙሉጌታ በርሄና ብ/ጄ መሃመድ ኢሻ እየተቀያየሩ ክ/ሩን አዘውታል። የክ/ጦሩ ስያሜና የነበረው ፍጭት በርከት ያሉ አዳዲስ አባላት በደብረ ዘይትና ብላቴ የኮማንድ ስልጠና ካጠናቀቁ በኃላ ከነባሮቹ የህወኃት ሻለቆች ጋር ውህደት ተደርጎ ክ/ጦር ሲመሰረት ስሙን እኛ እንድናወጣ ተነገረን፤ ይህንን የማስፈፀም ሃላፊነትም በተለይ ለኔ ተሰጠኝ። እኔም ስሙን እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመፈፀም አንድ ኮሚቴ አቆምኩ። ኮሚቴውን ከአማራ ኦሮሞና ትግሬ ተወላጆች በእኩል ደረጃ አደረኩ እና ወደ ስራው ገባን ስሙን በተመለከተ የተለያዩ አማራጩች ከነምክንያቶቹ ቀረቡ፤ ቴወድሮስ፣ ፈንቅል /የኃየሎም የበረሃ ስም ነው/ ፣ አግአዚ፣ ወልወል የተባሉ ስሞች ከነዝርዝር ምክንያታቸውና አስፈላጊነታቸው በጥቆማ ቀረቡ። ብዙ ውይይት አደረግንበት በመጨረሻ ሁለቱ ላይ ተጨቃጭቀን ተግባባን እና ሁለቱንም ለበላይ አካል እናቅርብና እነሱ ይወስኑ ብለን ተስማማን / ቴወድሮስና ፈንቅል/። ይህንኑ ለብ/ጄ ታደሰ ጋውና በወቅቱ የመከላከያ አስተዳደርና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኃላፊ ለነበረው አቀረብኩ።

እሱም ከነ ፃድቃን ጋር መክረውና ወስነው በቀጠሮ ጠራኝና ለክ/ጦሩ መጠሪያ አግአዚ እንዲሆን ከነ ምክንያቱ አስረዳኝ እና ይህንኑ ተቀብየ ወደ ክፍሌ ተመልሸ ለሚመለከታቸው ሁሉ ገለፃ አደረኩ። ክፍለ ጦሩ ከተመሰረተ በኃላ በአገር ውስጥ በደርግ የኮማንዶና አየር ወለድ ባለሙያወች በነ ጄ/ል ተስፋየ ኃብተማሪያምና ሻለቃ ታምሩ እና ሌሎችም እንዲሁም በውጭ በአሜሪካኖች ሩሲያውችና እስራኤሎች በተደጋጋሚ ስልጠና ተሰጥቷል። በተለያዩ ቦታወች በተለያየ ጊዜ በሞያሌ፣ ጅማ፤ ጋምቤላ፤ አሶሳ፤ ጅጅጋ፤ አሰበ ተፈሪ፤ አሩሲ፤ ሻሼ መኔ፤ አዋሳ፤ ጎዴ፤ ቀብዲዳሃር፤ አዲስ አበባ፤ ፍቸ፤ እና በሌሎችም ህዝቡ በመንግስት ላይ የመብት ጥያቄ ባነሳበት ሁሉ የህዝቡን መብት ለማፈን ክፍለ ጦሩ ግዳጅ እንዲፈፅም ተደርጉኣል። በተለይም ነባር አባሎች እንደምታስታውሱት በ1993 ህወኃት ከሁለት ሲሰነጠቅ ክ/ጦሩ በነፃድቃን ተፅኖ ስር ስለነበር በመለስ ላይ ታስቦ በነበረው መፈንቅለ መንግስት ለመጠቀም አዘጋጅተውት ነበር። ከነ ፃድቃን ውድቀት በኃላም ጀ/ል ሳሞራ የኑስ ቂም ይዞ ስለነበረው የኮማንዶ ጥቅማጥቅሙን እና የሚገባውን ትጥቅ እንኩአን እንደማይገባው /የፃድቃን ሰራዊት/ እያለ እስከ መተረብ ደርሶ እንደነበረ የምናስታውሰው ነው። ይህን ሃሳብ ለማንሳት የፈለኩት ክፍለ ጦሩን ከመጀመሪያም ለግል የስልጣን ፍላጎት መጠቀሚያ አስበው ያደራጁት እንደነበር ለማስገንዘብ ነው። መለስ ተቀናቃኞቹን ካስወገደና የሳሞራም ስልጣን ከተረጋጋ በኃላ አግአዚን ባለበት እንዲቀጥል ፈለኩት እንዲያውም ከላይ በጠቀስኩአቸው አካባቢወችና በሌሎችም የህዝብ ቁጣ ሲነሳ አጋአዚ በፍጥነት የህዝብን ጥያቄወች በኃይል ማፈን በመቻሉ የአመራር ለውጥ በማድረግ እንደገና ለማጠናከር ተንቀሳቀሱ። ክ/ጦሩ ከሻለቃ በላይ ያለው አመራር ፍፁም የትግሬ የበላይነት ያለው ቢሆንም ከሻምበል በታችና ተራ ወታደሩ ግን እስካሁን በቀዳሚነት የአማራ ተወላጆችና በተከታይነት የኦሮሞ ተወላጆች በዝተው ይገኛሉ። ይህ ማለት ለመጥፎም ለመልካምም ነገር ዋናውን ስራ የሚሰራውና ጠመንጃውን የያዘው ግንባር ቀደም ተሰላፊው ማን እንደሆነ በግልፅ እንረዳለን ።

በወያኔ ስርዓት ስርዓቱን በመቀዋወምና መብቱን በመጠየቅ በቀዳሚነት እየተንቀሳቀሰ ያለው ሰፊው የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ነው። የዚህን ህዝብ መብት በማፈን እና በመግደል ደሞ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ያለው አግአዚ ውስጥ ያለው የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው። በስራ ቆይታየ ከትግሬወች አንድ የተማርኩትና አሁን ላሉበት ሁኔታ ጠቅሟቸዋል ብየ የማስበው፤ በብዙ ነገር ሲጨቃጨቁ ሲጣሉ አያለው በትግራይ ህዝብ፤ ትግራዊነትና በድርጅታዊ ጉዳይ ግን አንድና አንድ ናቸው፡ ልዩነታቸውን ትተው መጥፎም ይሁን መልካም በጋራ ጉዳያቸው ላይ ብቻ ይረባረባሉ። በ1993 እነ ጀ/ል ፃድቃን ከመከላከያ በከባድ ሁኔታ ሲወጡ እነ መለስ የሚምሯቸው አይመስሉም ነበር / ሁኔታውም ከባድ ነበር እና/ ከወጡ በኃላ ግን ሁሉም በጡረታ /በክብር/ እና ዳጎስ ባለ ጉርሻ ጭምር ከነክብራቸው መሸኜታቸውን ስንሰማ ገርሞን ነበር። የ1997 ምርጫን ተከትሎ ወያኔ በምርጫ በደረሰበት ኪሳራ በተለይም የአማራውን ህዝብ ጥርስ እንደተነከሰበት ይታወቃል፤ በህዝቡ ብቻ ሳይሆን በስርዓት ውስጥ ባለን አማራወች ሁሉ ጥላቻቸው በግልጽ ይታይ ነበር። እኛም ሁኔታቸው ስላላማረን ራሳችን ለመከላከልና ሂደታቸውን ለመኮነን በፀረ-ህወኃትነት ተሰለፍን፤ ህወሃትን መክፈልም ይቻል ይሆናል ብለን በማሰብ ጀ/ል ፃድቃንን ለማነጋገር ወሰን /ጻድቃን ቀደም ሲል በሰርዊቱ የነበረውን ሁኔታ ተጠቅሞ አሁንም ተፅኖ ይፈትራል ብለን እናስብ ነበር። ሁለት ሁነን ፖሌ መድሃኒያለም ጀርባ ከፍቶት ከነበረው “የግጭትና ጥናት ምርምር” ምናምን የሚባል ቢሮ ከፍቶ ይሰራ ነበር። በደቡብ ሱዳንም የፀጥታ አማካሪ ሁኖ ለUN እና ለደቡብ ሱዳን መንግስት ይሰራ ነበር። እና ሰውየውን አግኝተን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ብዙ ከተነጋገርን በኃላ የመለስና የሳሞራ አካሄድ ወደ ጥፋትና ግጭት መንገድ እየሄዱ ስለሆነ ለምን ተባብረን አናስተካክለውም የሚል ጥያቄ አነሳንለት። እሱም ያነሳችሁት ልክ ነው ይገባኛል አሁን ግን ምንም ማድረግ አይቻልም ጊዜ መጠበቅ ይሻላል ይልቁንስ ከመከላከያ ውጡና ደቡብ ሱዳን በጥሩ ደመወዝ ልላካችሁ አለን። በዚያን ጊዜ በርካታ የትግሬ መኮነኖችን እንደላከና ተጠቃሚ እንዳደረገ እናውቃለን። እኛንም ብንፈልግ ሊልከን እንደሚችልም ተረድቶናል ግን ፍላጎታችን ያ አልነበረም።

በሌላ ጊዜ አንድ በጣም የምቀርበው ትግሬ ጄኔራል ጋር ስናወራ ስለ ፃድቃን አነሳን እና ጻድቃን እኮ በጣም አስተዋይ ነው እነ ገብሩ አስራት ህወኃት ላይ እንስራና መለስ እንዲወርድ እናድርግ ሲሉት እሱ ግን አይ በአሁኑ ሰዓት ለትግራይ ከመለስ የተሻለ የለም አላቸው። መለስም ይህንን ስለሚያውቅ በደቡብ ሱዳን ለUN አማካሪ መሆን እንደሚችል ፕሮፖዝ አደረገው ብሎ ነገረኝ። ሌላ ነገር ልጨምር በዚያው 93 በነበረው ልዩነት በርካታ ጀኔራሎች ፃድቃንን ተከትለው መለስን በመፈንቅለ መንግስት ለማስወገድ ከነ ተወልደ ወልደማሪያም ጋር ተሰልፈው ነበር፤ እነ ጀ/ል ገዛይ አበራ, ጀ/ል ሳረ መጆነን ጀ/ል ብርሃኔ ነጋሽ ጀ/ል አብርሃ ተወልደ ጀ/ል ዮሃንስ ገብረ መስቀል ኮል ተወልደ ፍስሃ እነዚህ ወሳኝ የአዛዥነት ቦታ ላይ የነበሩ ከነ ፃድቃን ቡድን ተሰልፈው የነበሩ ናቸው። ታዲያ ሁሉም ስህተታቸውን እንዲያምኑ ከተደረጉ በኃላ ለ3 ወር ብቻ ከነበራቸው ኃላፊነት አንዳንድ ደረጃ ብቻ ዝቅ ብለው ከቆዩ በኃላ ተመልሰው ወደ ነበሩበት የኃላፊነት ቦታ ተመለሱ። በአንፃሩ በውል እውነት መሆኑን ባላረጋገጡት ጉዳይ ላይ የእኛወቹን የአማራ መኮነኖች እነ ጀ/ል ኃይሌ ጥላሁን ጀ/ል ተፈራ ማሞ ጀ/ል አሳምነው ፅጌ ኮ/ል ደምሰው አንተነህ ኮ/ል መኮነን ወርቁ እና ሌሎችም በርካቶችን መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አስባችኃል በሚል ሰበብ በጭካኔ ተሰቃይተዋል ታስረዋል ቤተሰባቸውን በትነዋል። የ1997 ምርጫን ተከትሎ ሰራዊቱ ውስጥ ያለው /በአግአዚም ጭምር/ አማራና ኦሮሞ በጠላትነት ተፈርጆ ስንት ስቃይና መከራ እንደነበር ታውቃለህ። በአስር ሽወች የሚቆጠሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች የሰራዊት አባላት ታስረዋል በምርመራ ተሰቃይተዋል ያለምንም ጡረታና ድጎማ ተባረዋል። ይህ ሁሉ ሲደረግ የአንተ ዘር የሆነው አማራውና ኦሮሞው ተለይቶ እንጅ አንድም የትግሬ ተወላጅ ላይ የደረሰ ነገር አልነበረም።

ታዲያ ይህ ስርዓት የማን ነው ትላለህ? እኔም በነበረኝ የኮማንድ የአመራር አባልነቴ የትግሬ አመራሮች በክፍለ ጦሩ ይፈፀሙ የነበሩትን ዘረኝነትን ለመታገል ብዙ ብጥርም አልተሳካልኝም። የአመራር ምደባና የአደረጃጀት ለውጦች ባደረግን ቁጥር የሰው ኃይል ምደባ ላይ ከባድ ፍጭት እናደርግ ነበር። እነሱ ከላይ እስከ ታች አመራሩን ትግሬ እንዲይዘው ካላቸው ፍላጎት አንፃር ያስጨግሩኝ ነበር። እንዴውም አንዳንዴ የበላይ አካል ይወስነው ብለው እንድናልፈው ይደረግ ነበር ያው የበላይ አካሉ ሳሞራ ስለነሆነ እሱን ደግሞ እነሱ ስለሚያገኙት ጨዋታው ለነሱ ቀላል ነበር። በነሱ ጥርስ ውስጥም ሁኜ የአማራውን እና የኦሮሞውን ልጆች መብት በተወሰነ ለማስከበር የቻልኩ ቢሆንም ከኔ በኃላ ግን የአማራን እና የኦሮሞን አመራር ጠራርገው ወደ እግረኛ እንደላኩት እናንተም ታውቃላችሁ። ይህ ተጠራርጎ ወደ እግረኛ የተባረረው አመራር በብቃት ወይም በስነ-ምግባር ጉድለት ሳይሆን በዘሩና በማንነቱ ስላልተፈለገ ነበር። የትግራይ ገዥ መደብ የጭቆና አገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም በዋነኛነት አንተን በመሳሪያነት በመጠቀም ለመብቱና ለነፃነቱ ሰላማዊ ጥያቄ ያነሳውን የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን ዕድታፍንና ወገንህን እንድትገድል እያደረገህ ነው። እነሱ እንወክለዋለን እንጠብቀዋለን እናበልፅገዋለን ብለው የተነሱለን የትግራይን ህዝብ በሰላም እያኖሩ አንተ የተፈጠርክበት የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ግን በአንተና በአገዛዙ ታጣቂወች በየቀኑ ይገረፋል ይታሰራል ይገደላል።
ለምን ብለህ ማሰብና ማሰላሰል ይኖርብሃል! ከጨካኞች የባዕድ ገዥወች ወግነህ የራስክን ወገን ከመጨፍጨፍ ወገንህን መከላከል ታሪካዊ ግዴታህ ነው። እንደምትረዳው በአሁኑ ሰዓት የዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በመንኮታኮት ላይ ሲሆን በአንፃሩ የህዝቡ የነፃነት ትግል ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህንን እየሞተ ያለ ብስባሽ ጨርሶ ለመቅበር ከአንተ ከአግአዚ የአማራና የኦሮሞ አባላት የሚከተሉትን እንድትፈፅም በሚጨፈጨፈው ወገን ስም እጠይቃለው።

1ኛ. አንተም ሆንክ የመከላከያ ሰራዊቱ ዋነኛ ግዳጅ ዳር ደንበር መጠበቅ እንጅ ሰላማዊ ወገንህም መጨፍጨፍ አይደለም። ስለሆነም ከተልኩአችን ውጭ ሰላማዊ ህዝባችን ላይ አንዘምትም በል።
2ኛ. የህዝብ ልጅ ነህና ህዝብ የጠየቀውን የመብት ጥያቄ አንተም ጠይቅ፣ መሳሪያህን አስቀምጠህ ከህዝቡ ጋር አብረህ ጩህ።
3ኛ. በጦር ክፍልህ ውስጥ በእርስትነት በትግሬወች የተያዘውን የአመራር ቦታ ይገባኛል በል። በቃ ሁል ጊዜ በትግሬ አልታዘዝም በል።
4ኛ. በየደረጃው ያሉት የትግሬ አዛዞች የሚፈጽሙትን ሙስና እና ብልግና ያለ ምህረት አጋልጥ ታገል።
5ኛ. በየቦታው ህዝብን እንድትጨፈጭፍ የሚሰትህን ግዳጅ እምቢ በል፣ በኃይል ፈፅም ከተባልክ መሳሪያህን በትግሬ አዛዝ ላይ አዙረው።
6ኛ. ከላይ ያልኩአቸውን ነገሮች በድፍረት ተግባራዊ አድርጋቸው፣ በዚህ የማይተረሙ ከሆነ ከሌሎች ከሚመስሉህ ጋር ተነጋገር ከነ ሙሉ ትትቅህ ወደ ህዝብህ ተቀላቀል።
ወገኖቸ እስካሁን አውቃችሁም ይሁን ሳታውቁ ወገናችሁን አድምታችኃል ገድላችኃል፣ አሁን ግን በቃን በማለት የበደላችሁትን ወገናችሁን በመካስ ታሪካችሁን አድሱ። ወያኔ እየተንኮታኮተ ያለ ወንጀለኛ ቡድን ነው፣ ለዚህ ደመኛ የህዝብ ጠላት መጠቀሚያነታችሁ ይብቃ። ዛሬውኑ ወስኑና ንስሃ ገብታችሁ ወደ ህዝባችሁ ወግኑ።  አለበል አማረ /ኮሎኔል/

No comments:

Post a Comment

wanted officials