Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 17, 2016

በግብፅ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ150 በላይ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በግብፅ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ150 በላይ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢሳት (ነሃሴ 10 ፥ 2008)
በግብጽ የሜዲትራኒያን ባህር ግዛት ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት በህገወጥ መንገድ ሲጓዙ ነበሩ የተባሉ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ150 በላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ስደተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የግብፅ የባህር ሃይል ባለስልጣናት አስታወቁ።
በሃገሪቱ በኩል ወደ አውሮፓ ለመሰደድ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ድርጊቱ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ዴይሊ ኒውስ ኢጂፕት የተሰኘ ጋዜጣ ባለስልጣናትን ግቢ በማድረግ ዘግቧል።
በቁጥጥር ስር የዋሉትን 153 ስደተኞች ከኢትዮጵያ፣ ግብፅ ኤርትራ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ ሲሆኑ፣ ስደተኞቹ ተላልፈው መሰጠታቸውን የባህር ሃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ሞሃመድ ሳሚር ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
ባለፈው ወር በተመሳሳይ ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 143 የጎረቤት አፍሪካ ስደተኞች በግብፅ የሜዲትራኒያን የባህር ግዛት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።
ሃገሪቱ ለአውሮፓ ስደት አዲስ መንገድ እየሆነች መምጣቷን የተናገሩት የግብፅ የባህር ሃይል ባለስልጣናት የስደተኞቹን ጉዞ ለመግታት መጠነ ሰፊ የቁጥጥር ዘመቻ መክፈቱን አስታውቀዋል።
ከወራት በፊት በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ወደ ሃገሪቱ በስደት መግባታቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ይገልጻሉ።
ወደ ሃገሪቱ በስደት ከገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል ሁለቱ ባለፈው ወደ ራሳቸውን በማቃጠል ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
የሁለት ልጆች እናትና አንድ ወጣት የወሰዱት ይኸው እርምጃን ተከትሎ ሃዘን እንደተሰማው የገለጸው የስደተኛ ኮሚሽን ቢሮው ከተወሰኑ ቀናት አገልግሎት አቋርጦ እንደንበር የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ሲዘግቡ ቆይተዋል።
የአለም አቀፉ የስደተኞች ኮሚንሽንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኢትዮጵያ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር እየተባባሰ መምጣቱን በመግለጽ ላይ ሲሆኑ መንግስት ስደተኞቹን ለመቆጣጠር በድንበር የሚያካሄደው ቁጥጥር ችግሩን አለመቅረፉ ይነገራል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials