Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 31, 2016

በጎጃም የደምበጫና አማኑኤል ሕዝብ በሕወሓት መንግስት ላይ ተነሳ | የቋሪት ሕዝብ የራሱን የጎበዝ አለቃ መረጠ

በጎጃም የደምበጫና አማኑኤል ሕዝብ በሕወሓት መንግስት ላይ ተነሳ | የቋሪት ሕዝብ የራሱን የጎበዝ አለቃ መረጠ
የጎጃም ሕዝብ የአማራ ተጋድሎ እንደቀጠለ ነው:: ዛሬ በጎጃም ደምበጫ እና አማኑኤል ከተሞች ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ ተነስቷል:: እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ በም ዕራብ ጎጃም ደምበጫ ከተማ የጸረ ሕወሓት መንግስት ትግሉ አይሏል::
ደምበጫ ሕዝቡ አደባባይ በመውጣት የትግራይ ተገንጣይ ሥርዓት ሃገሪቱን ጥሎ እንዲወጣ ጠይቋል:: ሕዝቡ በተቃውሞም ተምጫ ድልድይን የዘጋው ሲሆን ማንኛውም ትራንስፖርት በዚህ ድልድይ በኩል እንዳያልፍ አድርጎ ስር ዓቱን እየተቃወሙ ነው:: “ወልቃይት አመራ ነው; ሕወሓት ጸረ አማራ ነው” የሚሉ መፈክሮች እየተሰሙ ነው::
በሌላ በኩል አርሶ አደሮች ዛሬ የገበያ ቀን ቢሆንም ከተማ ውስጥ ከገቡ አብረው ሊበጠብጡ ይችላሉ በሚል የትግራይ ተገንጣይ መንግስት ወታደሮች ወደ ደምበጫ ከተማ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል::
በሌላ በኩል ቤተ አማራ እንደዘገበው በምስራቅ ጎጃሟ አማኑኤል ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡ በደ/ማርቆስ ትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ሰራዊት መኪና ላይ ከባድ መትረይሶችን በመደገን ያልተጠበቀ ሰልፍ ሊካሄድ ይችላል በሚል እሳቤ ከተማዋን ወረዋታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከአዲስ ኣበባ የመጡ የህዝብ ባሶች ከኣማኑኤል ጀምሮ እየተደረገ ባለው ተቃውሞ ደብረማርቆስ እንዲያድሩ ተደርጓል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ደርግን ለመጣል ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው የቋሪት ሕዝብ በዛሬው ዕለት ከፍተኛ ስብሰባ በማድረግ የሚመራውን የጎበዝ አለቃ መምረጡ ተሰማ:: የቋሪት ሕዝብ ከሕወሓት መንግስት ነጻ እስካልወጣን ድረስ በነርሱ አንገዛም; ትግላችንም እስከመጨረሻው ድረስ ነው ሲል ቃል በመግባት መሪዎቹን መርጧል:: በየክልሉ ያሉ የነጻነት ታጋይ ሕዝቦች ከቋሪት ነዋሪዎች ተምረው እንዲሁ የራሳቸውን የጎበዝ አለቃ እንዲመርጡ በተደጋጋሚ በፖለቲከኞች ሲመከሩ እንደነበር አይዘነጋም::((ዘ-ሐበሻ) )

No comments:

Post a Comment

wanted officials