Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 16, 2016

በኬንያ ወህኒ ቤት ለአራት ወራት የማቀቁት ኢትዮጵያዊያን ‹‹ድረሱልን››እያሉ ነው


ከኢትዮጵያ ደቡባዊ ክፍል ተነስተው ‹‹ስራና የተሻለ ህይወት ፍለጋ›› ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት በሞያሌ በኩል ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ የገቡት ሰባቱ ወጣቶች በዋና ከተማይቱ ናይሮቢ ፖሊሶች እጅ በመውደቃቸው ውጥናቸው አልተሳካም፡፡
ፖሊሶቹ ወጣቶቹን ሰብስበው ‹‹ወደአገሪቱ ያለፈቃድ በህገ ወጥ መንገድ በመግባት ››የሚል ክስ መስርተው ፍርድ ቤት አቆሟቸው፡፡ፍርድ ቤቱ ወጣቶቹን ስራና የተሻለ ህይወት ፈላጊዎች ጥፋተኛ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ በማለቱም የ300 ዶላር ቅጣት ወይም የስድስት ወራት እስራት በየነባቸው፡፡ቅጣቱን በገንዘብ ለማስለወጥ አቅም ያልነበራቸው በመሆኑም ያለፉትን አራት ወራት በናይሮቢ ካሳራኒ የፖሊስ ጣቢያ አሳለፉ፡፡
አሁን የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ቢሆንም ፖሊስ ወደአገራቸው ሊመልሳቸው ባለመቻሉ ከፍርድ ውጪ በወህኒ ቤቱ እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡ህዝቡና ቤተሰቦቻችን ያለንበትን ሁኔታ እንዲያውቁልን አድርግ በማለታቸውም ስማቸውን ከዚህ በታች ዘርዝሪያለሁ፡፡
ተከተል በየነ
ጌታቸው በቀለ
ጽንሰት አለሙ
ጀማል አህመድ
አረጋ እርሴሎ
ኦሳቦ ጎዴቦ
ካሚቲ መዲም
ወጣቶቹ በሙሉ ከአንድ አካባቢ ከሆሳህና የመጡ መሆናቸውን በመግለጽ ቤተሰቦቻቸውን የሚያውቅ ሰው ያሉበትን ሁኔታ እንዲነግርላቸው ይማጸናሉ፡፡ወጣቶቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ከህገ ወጥ እስራቸው እንዲፈቱ የቻልነውን ያህል ድምጽ እንድንሆናቸውም በአክብሮት ይጠይቃሉ፡፡

13718112_608021232696544_729113258_o

No comments:

Post a Comment

wanted officials