Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, August 27, 2016

ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች የህወሓትን መንግስት እየገመገሙ ነው::


በህወሓት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት በዲፕሎማቶች እየተገመገመ መሆኑ ተሰማ፡፡ በአዲስ አበባ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ በሀገሪቱ ከልዩ የፖሊስ ኃይል በተጨማሪ ከፍተኛ መጠን ያለው የታጠቀ መከላከያ ሠራዊት ከተማዋን ወርሯት ነበር፡፡ ትላንት ይካሔዳል ተብሎ እቅድ ተይዞለት የበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ለዜጎቻቸው የተጠንቀቁ መልዕክት ያስተላለፉት የምዕራብ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ ወቅታዊውን የሀገሪቱን ሁኔታ በንቃት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ መንግስት የተነሳበት ህዝባዊ ተቃውሞ በከፍተኛ መጠን እንደከበደው ይታያል፡፡ ከዚህ ቀደም በተወሰነ የፖሊስ ኃይል ይቆጣጠራቸው የነበሩ ህዝባዊ ተቃውሞዎች አሁን ላይ መከላከያ ሠራዊት እስከማሰለፍ አድርሶታል፡፡›› ሲሉ የገለጹት ዲፕሎማቶቹ፣ የኢትዮጵያን መንግስት በመደጎም ግንባር ቀደም የሆኑ ሀገራት፣ ስርዓቱ ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር ወደ ድርድር እንዲገባ ግፊት ለማድረግ ነገሮችን እየገመገሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ከዚሁ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ፤ የአሜሪካ ዓለም ዓቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ዊስሊ ሬድ ‹‹ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በኢትዮጵያ ዜጎች ድምጻቸው እንዲሰማ እንደሚፈልጉ ተመልክተናል፡፡ በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉት እና በጎዳና ላይ ሰልፍ የወጡ ዜጎች እርስ በእርስ እንዲደማመጡ አሳስባለሁ፡፡ ሀሳቡን በመግለጹ ብቻ ማንም ሰው መሞት የለበትም፡፡›› ሲሉ አዲስ አበባ ተገኝተው አሳስበዋል፡፡
ሚስ ዌስሊ ሬድ ያስተላለፉት መልዕክት ሀገራቸው አሜሪካ በኢትዮጵያ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ያላትን አቋም የሚያመለክት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም እስከሚቀጥለው የካቲት 2017 ድረስ የሚቆይ የጉዞ እና የደህንነት ማስጠንቀቂያ መግለጫ አውጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከተቃዋሚዎቹ ጋር ለድርድር እንዲቀመጥ ምዕራባውያን ሀገራት ጫና ለማድረግ እንደተዘጋጁ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ቢቢን

No comments:

Post a Comment

wanted officials