Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 9, 2016

አዳማ / ናዝሬት :- የአማራ ሕዝብ ጥቃት የኛ (የኦሮሞ ሕዝብ) ጥቃት ነው

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኣፌኮ እና የሰማያዊ መሪዎችን፣ አቶ ይልቃል ጌትነትና ዶር መራራ ጉዱናን ለአስቸኩዋይ ስብሰባ ጠራ።በጎንደር አከባቢ ባለው ሁኔታ የተነሳ የትግራይ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን ቅጥር ግቢ ለቀው እየወጡ ነው የሚል ሪፖርት ደርሶናል። የኦሮሚያ ተማሪዎችም እንዲወጡ የተነገራቸው ቢሆንም እስካሁን የተጋረጠብን አደጋ የለም፤ ከህዝቡም ጋር ምንም ቅሬታ የለንም፤ የሚያስኬደን ምክንያት የለም በማለት ለመቆየተ ወስነዋ። የጎንደር ብሎም የአማራ ክልል ህዝብ የተማሪዎች ከተናካሽ ወያኔዎች እንደሚታደጋቸው ተስፋ አለን።
ባህር ዳር በፈለገ ህይዎት ሆሥፒታል ውሥጥ 5 ሠዎች አሥከሬናቸው ይገኛል። የሞቱትን ሠዎች ሥምና አድራሻቸውን ማወቅ እንዳልተቻለ ተገልጿል። መታወቂያ ወረቃታቸው ሆነ ተብሎ እንደተወሠደም ነዋሪዎቹ ያምናሉ። የሞቱት ሠዎች ወጣቶች ሲሆኑ ከጎንደር አካባቢ የመጡ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገምቷል!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials