Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, August 7, 2016

በደብረታቦርና በጋይንት ሕዝብ በነፋስ መውጫ ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሔደ







ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓም  እኩለ ሌሊት ላይ የአገዛዙ ቅጥረኞች በየመንደሩ እየዞሩ በድምጽ ማጉያ ወደ ተጋድሎ ሰልፉ የከተማው ነዋሪዎች እንዳይሔዱ ሲያስጠነቅቁ ቢያድሩም የደብረ ታቦር ዐማሮች ገና ጠዋት 12 ሰአት ሳይሆን ገንፍለው ወደ አደባባይ ወጥተዋል፡፡ ከቦታው ባገኘነው መረጃ መሠረት ወደ 100 ሺህ የሚጠጋ ሕዝብ ከቴዎድሮስ አደባባይ ተነስቶ የጋሳይና የክምር ድንጋይ ዐማሮችን ለመቀበል ወደ ጎማጣን አልፎ ሒዷል፡፡
በአስለቃሽ ጢስና ተኩስ ለመበተን የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። የዳሽን ቢራ የማስታወቂያ ቢልቦርድ ከተሰቀለበት ወርዶ ተሰባብሯል።
የጋሳይና የክምር ድንጋይ ከተማ ዐማሮች ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሲሆን የደብረ ታቦር ዐማሮችን ለመቀላቀል እየመጡ መንገድ በወያኔ ቅጥረኞች ተዘግቶ በመታገል ላይ ናቸው፡፡ በሰልፉ ላይ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ በዋናነት እየተስተጋባ ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የፌደራል ፖሊስ በደብረ ታቦር ዐማሮች ላይ የአስለቃሽ ጢስና የጥይት እሩምታ ቢከፍትም ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ የተጋድሎ ድምጹን እያሰማ ነው፡፡ ከወረታ፣ አዲስ ዘመንና እብናት የተጋድሎው ተሳታፊዎች    ፡፡

የጋይንት ዐማሮች በዙሪያቸው የከበበውን የወያኔ ፀጥታ አስከባሪ ከምንም ሳይቆጥሩ ለተጋድሎ መውጣታቸው ታውቋል፡፡ የጋይንት ሕዝብ በነፋስ መውጫ ከተማ ዋና መንገድ ሰልፍ እያካሔደ ይገኛል፡፡ ሳሊ፣ ጎብጎብና የጨጭሆ ከተማዎችም ላይ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ መኖሩ ነው የሚሰማው፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials