Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 10, 2016

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በጀርመን ፍራንክፈርት ለአርብ ነሃሴ 06 2008ዓም /12 08 2016



ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን
በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ በንጹሃን ኦሮሞ እና አማራ ህዝብ የመንግስት ታጣቂዎች እየፈጸሙ ላሉት የነፍስ መገደል እና እስራት በመቃወም በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ድምጻቸውን ለአለም ለማሰማት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት በጋራ ለአርብ ነሃሴ 06 2008ዓም 12 08 2016 ጥሪ አስተላልፉዋል። ይህ የተቋሞ ሰልፍ በበርሊን ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ፤ለአመቺነቱ በፍራንክፈርት ከተማ እንዲሆን ተወስኗል። በዚህም ሰልፍ ጥቁር በመልበስ በመላው ኢትዮጵያ በወያኔ ጦር በግፍ ህይወታቸውን ላጡት ለንጹሃን ዜጎቻችን የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንግለጽ።


የሰልፉ አላማዎች


1ኛ የወያኔ ኢህአዲግ በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ በማጋለጥ


2ኛ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በወያኔ ላይ ተጽእኖ እንዲያደርግ በመታገል



3ኛ አለአግባብ የታሰሩ የህዝብ ተወካዮች ጋዜጠኞች የፖለቲካና የሀይማኖት መሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ


4ኛ ወያኔ ኢህአዲግ ሃገሩንና ህዝቡን ማስተዳደር ስላልቻለ በአስቸኩዋይ ከስልጣን የሚወርድበትን እንዲሁም ስልጣኑን ለህዝብ አስረክቦ የሽግግር መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ መጠየቅ ናቸው።


ሰልፉ የሚጀምርበት ሰዐት: -12:00


ሰልፉ የሚጠናቀቅበት ሰአት:-17:30


የሰልፉ መነሻ ቦታ:- ፍራንክፈርት ሀብት ቫኸ (Frankfurt Hauptwache)


ሰልፉ የሚጠናቀቀው:-ኢትዮጵያ ኢምባሲ በር ላይ

No comments:

Post a Comment

wanted officials