Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 31, 2016

በካምፓላ የወያኔ ደጋፊዎች ተደናግጠዋል




ነሃሴ 19/2008 ዓ/ም በአንድ ወጣት ደራሲ የተደረሰ መጸሃፍ ካምፓላ ላይ ተመረቀ!
የካምፓላ ምንጮቻችን እንደነገሩን መድረኩም በእውነተኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆ ነበር። ምሽቱን ልዩ ያደረገው አጋጣሚ ቀንደኛ የወያኔ ወዳጆችም ሳይቀሩ በምረቃው ላይ ታይተዋል። “ወልቃይት የትግራይ ነው! መተማ ደሞ የሱዳን ነው ! “ያለው የወያኔ ቤተኛ ማርቆስ ጌትዬ ስደተኛ መስሎ መገኘቱ ታውቋል።የወያኔ ኤንባሲ ባደራጀውና ስደተኞች ሳይቀሩ አባል በሆኑበት የዲያስጶራ ኮሚኒቲ ሰብሳቢ አቶ ስለሺ ፀጋዬም ተሳትፏል።በምሽቱ ሃገር ወዳድ ወጣቶች ባቀረቡት ዝግጅት በርካቶች ደስተኞች እንደነበሩና አቶ ስለሺም በስሜት ተነስቶ በማንባት የፕሮግራሙን አዘጋጆች አመስግኗል። ከእንግዲህም ከወያኔ ኤንባሲ ጋር እንደዱሮው በወዳጅነቱ የማይቀጥልበት ደረጃ ላይ መድረሱንም የዐይን እማኞች ተናግረዋል። የመጸሃፉ ደራሲ ናቲ ቪሎፒያ በሲዲ ጭምር ያዘጋጀው የጥበብ ስራውን በምሽቱ ያስመረቀ ሲሆን አክቲቪስት ታማኝ በየነ የላከው የቪዲዮ መልዕክት በምሽቱ ቀርቧል። በሃገር ቤት በወያኔ አጋዚ የተጨፈጨፉ ወገኖችንም ሻማ በማብራት ተዘክረዋል። ይህን ስብሰባ ተከትሎ የወያኔ ኤንባሲ በምሽቱ በመፀሃፍ ምረቃው ላይ የተገኙትን ወዳጆቹን በምስጢር ለሃሙስ ስብሰባ እየጠራ መሆኑንና በድርጊቱም መደናገጥና ብስጭት እንደሚታይባቸው ስልክ ተደውሎ ከተጠሩት መካከል የተገኘው መረጃ ጠቁሟል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials