ባህር ዳር ከተማ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የማሳወቂያ ደብዳቤ ገቢ ተደረጓል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 01 ቀን 2008 ዓ/ም በባህር ዳር ከተማ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ ከሀሙስ ሐምሌ 21 ቀን 2008 ዓ/ም ጀምሮ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ተቀብሎ ምላሽ እንዲሰጠን በተደጋጋሚ ጊዜ ጠይቀን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆንም ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2008 ዓ/ም ለባህርዳር አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት፣ ለመምሪያ ፖሊስ እና ለፀጥታ ዘርፍ አስፈርመን አስገብተናል፡፡በመሆኑም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ማሳወቅ በቂ በመሆኑ ሰልፉ እሁድ ነሀሴ 01 ቀን 2008 ዓ ም በባህር ዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ስለሚካሄድ የባህር ዳር ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፉ እንድትሳተፉ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

No comments:
Post a Comment