Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 5, 2016

የቱኒዚያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን እንዲለቁ ድምፅ ሰጠ

የቱኒዚያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን እንዲለቁ ድምፅ ሰጠ

የቱኒዚያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን እንዲለቁ ድምፅ ሰጠ
የቱኒዚያ ፓርላማ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀቢብ ኤሲድ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ድምፅ ሰጥቷል።
ከ191 የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት ውስጥ 188 አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀቢብ ኤሲድ ስልጣን ይልቀቁ በሚል ድምፅ የሰጠ ሲሆን፥ ሶስት የፓርላማ አባላት ብቻ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ፓርላማው ከዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገው፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀቢብ ኤሲድ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ለውጥ ማምጣት ባለመቻላቸው ነው ተብሏል።
ይህንን ተከትሎም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ እምነት ያጣው የሀገሪቱ ፓርላማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲለቁ ሲል በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።
የቱኒዚያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ለ2 ዓመታት ያገለገሉት ሀቢብ ኤሲድ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ለውጥ ማምጣት አልቻሉም በሚል ትችት ሲሰነዘርባቸው መቆየቱ ይታወሳል።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቤጂ ካይድ ኤሴቢ ባለፈው ወር ላይ የቱኒዚያ የጥምር መንግስት በሀገሪቱ የተጋረጠውን የኢኮኖሚ ችግር በጋራ በመሆን መፍታት አለባቸው በማለት ጥሪ አስተላልፈው ነበር።
በቱኒዚያ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 ከተቀሰቀሰው አብዮት ወዲህ በሀገሪቱ የስረራ አጥነት ችግር በከፍተኛ ቁጥር እየጨመረ መሆኑም ይነገራል።
በአሁኑ ጊዜም በርካታ የቱኒዚያ ወጣቶች ስራ አጥ ሆነው መቀመጣቸውም ነው የሚነገረው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

No comments:

Post a Comment

wanted officials