ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008)
በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች ህዝባዊ እምቢተኝነት ተጋግሎ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በመንግስት ሃይሎች ጥቃት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን አጋርነታቸው ለማሳየት ጸጉራቸውን መላጨታቸውን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ።
ኢትዮጵያውያን ጸጉራቸውን ሲላጩ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ደረገጾች መለቀቃቸውን ያወሳው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የእንግሊዝኛው አገልግሎት፣ የጸጉር መላጨት ድርጊት የታሰሩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ የተፈጸመ መሆኑን አስረድቷል።
በኢትዮጵያ ጸጉር መላጨት ሃዘንን መግለጽ ነው ያለው ሌላው የዚምባብዌ ጋዜጣ፣ ድርጊቱ በኦሮሞያና በአማራ ክልሎች በመንግስት ሃይሎች በተደረጉ ግድያዎች የሞቱትን ዜጎች ለማስታወስ የተደረገ መሆኑን ገልጿል።
በኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ከ500 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የገለጸው የአሜሪካ ሬዲዮ የእንግሊዝኛው አገልግሎት፣ ህዝባዊ ተቃውሞውን ያስተባብራሉ የተባሉ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ጭምር በጨለማ ወህኒ ቤት መወርወራቸውን አብራርቷል።
በተለያዩ ክልሎች ለዴሞክራሲ፣ ፍትህና ነጻነት ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖችን ለማስታወስ ኢትዮጵያውያን ከነሃሴ 19 እስከ 21 ፣ 2008 የሚቆይ የሶስት ቀን ብሄራዊ ሃዘን እንዲታወጅ በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ እስረኞች መጠየቃቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው።
ብሄራዊው የሃዘን ቀን በኦሮሚያና የአዲስ አባባና ፊንፊኔ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን በመቃወም፣ በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማንንነትና የድንበር መካለል ጉዳይ፣ በጋምቤላና በደቡብ ክልሎች፣ በኮንሶ ብሄረሰብ እንዲሁም በሌሎች የሃገሪቷ ክፍሎችም የስርዓቱን አፈና በመቃወም ጥያቂያቸውን አንግበው አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ ዘግናኝና ጅምላ ጭፍጨፋ ለማስታወስ እንደታወጀ በእስር ቤት የሚገኙ እነ አቶ በቀለ ገርባ መጥራታቸው መዘገባችን ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment