Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 9, 2016

ለአስር በመደራጀት ለቡድኑ አንድ የጎበዝ አለቃ በመመረጥ ትግሉን እናቀላጥፈው



(የጎበዝ አለቃ አስፈላጊነት) ከሙሉቀን ተስፋው
ሰው በመደራጀት ለቡድኑ አንድ የጎበዝ አለቃ በመመረጥ ትግሉን እናቀላጥፈው

የተጋድሎ የመኖር መብታችንና ሕልውናችን እስኪረጋገጥ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ይህ ተጋድሎ የ ሕዝብ ነው፤ በማንም ጣልቃ ገብነት የተመራ አይደለም፡፡ ሕዝቡ ነው እየተጋደለ ያለው፤ ባለቤትነቱም የ ሕዝብ ነው፡፡


በሁሉም አካባቢዎች ተጋድሎው ተቀጣጥሏል፤ መቆም የሚችል አይደለም፡፡ ከዚህ በኋላ በምንም መልኩ ወደ ኋላ የሚል አንድም የለም፡፡ በያዝነው ሳምንት ሲጠባበቁ የነበሩ የወሎና የሸዋ አካባቢዎች ተጋድሎውን ለመጀመር ቀናትን ቆርጠዋል፡፡ በዚህ ሳምንት የየከተሞችን መርኃ ግብር እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል፡፡ ሆኖም የዐማራን ሕዝብ ተጋድሎ ቀጣይነት ለማረጋገጥ በርካታ መሠራት ያለባቸው ነገሮች አሉ፡፡

1. በሰለማዊ ሰልፍ ሰበብ የሚሞቱ ችን ቁጥር መቀነስ አለብን/ መኖር የለበትም፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለው እያንዳንዱ ራሱን የመከላከል መብት ሲጠቀም ብቻ ነው፡፡ ሊገድለው የመጣን ጠላት እጅን አጣጥፎ በመቆም ሰውነትን ለጥይት መስጠት የእኛም የአባቶቻችንም ታሪክ አይደለም፡፡ ሒዱ በላይ ዘለቀን ጠይቁት? ፊታውራሪ ገብርየ ያደረገው ምን ነበር? ጀግናው ኃይለ ማርያም ማሞ ምን ሠራ? እያልን እንጠይቅ፡፡ ጠላታቸውን ግንባር ግንባሩን እያሉ ነው ያደባዩት፡፡ እኛስ የማን ልጆች ነን?

2. በሁሉም አካባቢዎች ለተጋድሎ የሚወጡ ሰዎች ጎበዝ አለቃን መምረጥ አለባቸው፡፡ እነዚህ ጎበዝ አለቃዎች ሲመረጡ አመራር የመስጠት ብስለት ያላቸው፤ ለዐማራው ሕዝብ እስከ ሞት ድረስ የታመኑ መሆን አለባቸው፡፡ ማንኛውም የዐማራ ገበሬ ያለውን ነፍጥ መጠቀም አለበት፡፡

3. የሚመረጡ የጎበዝ አለቆች ማንኛውም ዓይነት የስልክ፣ የኢንተርኔትና የመገናኛ ዘዴ ሁሉ እስከ ድል ቀን ድረስ በወያኔ እጅ ያለ በመሆኑ ሊቋረጥ እንደሚችል በመገንዘብ በቅርበት ካሉ ተጋድሎዎች ጋር ባሕላዊ የግንኙነት ዘዴን መፍጠር አለባቸው፡፡ ለምሳሌ በሚስጥር ደብዳቤ በመጻጻፍ ሊሆን ይችላል፡፡

4. በሁሉም አካባቢዎች በገጠርና በከተማ የተጋድሎ ክተት አዋጅ ነጋሪት ተመቷል፡፡ ሕዝብ ዘርህን ለማትረፍ በየጎጡ በሳል የጎበዝ አለቆችን በመምረጥ ቀያችንን ከወያኔ ነጻ ማድረግ አለብን፡፡ ሁሉም በተመሳሳይ ቀንና ሰአት፣ ለረዥም ዘመን ከተጋደለ ወያኔ ምንም ማደረግ አይችልም፤ እንዲያውም ከእግርችን ሥር ይውላል፡፡

5. ሁሉም ሕዝብ ከውጭ የሚመጣ ማንኛውም ዓይነት እርዳታ እንደሌለ ተገንዝቦ በራሱ ኃይልና ጥረት ተጋድሎውን ማፋፋም አለበት፡፡ ተጋድሎውን ሊያኮላሹ የሚችሉ በርካታ ኃይሎች እንዳሉ በመገንዘብ የራሱን ሕልውና ራሱ ማስጠበቅ አለበት፡፡

6. በመከላከያ ሠራዊት፣ በፌደራልና በክልል ፖሊሶች በልዩ ልዩ ቦታ ያሉ ልጆቻችሁን፣ ወንድሞቻችሁንና ዘመዶቻችሁን ሥራቸውን እያቆሙ ከወገኖቻቸው ጋር እንዲሠለፉ አድርጉ፡፡ ሆድ አደር ሆነው የሚቀሩ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ግን የትም አይደርሱም፡፡

7. በተጋድሎ ወቅት የ ሕዝብ ንብረት የሆኑ ንብረቶች ላይ የሚደርሱ ውድመቶችን መከላከል አለባችሁ፡፡ ለምሳሌ የጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የግለሰቦችን ንብረት ውድመት መከላከል አለብን፡፡ የ ሕዝብ ሊያወድማቸው የሚገባቸው የሥርዓቱ መገልገያ የሆኑ የአገዛዙም ይሁን የግለሰብ ንብረቶችን ብቻ ነው፡፡

እያንዳንዱ ማኅበራዊ ሚዲያ የሚጠቀም ማኅበረሰቡን ለተጋድሎ ማንቃት አለበት፡፡
በውጭ አገር የሚኖሩ ዐማሮች በአገር ቤት ወገኖቻቸው ላይ የሚደርሰውን እልቂት ለመመከት ሊኖራቸው የሚችለውን አስተዋጽኦ በተመለከተ የውይይት መድረኮች እየተዘጋጁ ስለሆነ በዚሁ በንቃት ተሳታፊ መሆን አለባቸው፡፡







ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው::

No comments:

Post a Comment

wanted officials