Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 2, 2016

የእከክ በሽታ በአዲስ አበባ መከሰቱ ተሠማ፡፡



ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በውሃ እጥረትና በንፅህና ችግር ምክንያት የእከክ በሽታ በወረርሽኝ ደረጃ ተከስቶ የነበረ ቢሆንም የክረምቱ ዝናብ ከጀመረ በኋላ ቁጥሩ ቀንሷል ተባለ…

በአማራ ክልል ብቻ በድርቅ ከተጎዱ 86 ወረዳዎች ነዋሪ የሆኑ 400 ሺህ ያህል ሰዎች በእከክ በሽታ መያዛቸውን ሰምተናል፡፡


በዋግ ህምራ ዞን፣ በደቡብ ወሎና በምሥራቅ ሸዋ አካባቢ ሁኔታው አሳሳቢ እንደነበርም ከክልሉ ጤና ቢሮ ሰምተናል፡፡

በአለርት ሆስፒታል የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ሃኪም የሆኑት ዶክተር ድጋፌ ፀጋዬ በበኩላቸው የእከክ በሽታ በድርቅ ከተጎዱ አካባቢዎች ባለፈ ተላላፊ በመሆኑ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥም ተከስቷል፡፡

ለበሽታው የሚያስፈልገው ዋና መድኃኒት ግን በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ከጠፉ የሚቀቡ ፀረ ባክቴሪያ የቆዳ ማከሚያ መድኃኒቶች መካከል አንዱ ነው ብለዋል፡፡

በአማራ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ተወካይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌታነህ ደሳለኝ ለሸገር እንደተናገሩት የእከክ በሽታ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች እስካለፈው ግንቦት ወር ድረስ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነበር ብለዋል፡፡

400 ሺህ ሰዎችም በበሽታው ተጠቅተው የነበረ ሲሆን የመድኃኒት እጥረትም እንደነበር አልሸሸጉም፡፡ በኋላ ግን መድኃኒቱ በሃገር ውስጥ እንዲመረት መደረጉንና በቂ ዝናብ እየዘነበ በመሆኑ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀንሷል ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials