Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, July 9, 2016

የ12ኛ ክፍል ሃገራቀፍ ፈተና መሰረቅ ተከትሎ በርካታ ቀውስ ፈጥሯል ኣልፈዋል ኣሁንም እየፈጠረ ነው።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ጉዳይ !
የፈተናው መሰረቅ ተከትሎ መንግስ የራስ መተማመን መንፈሱ የተሸመደመደ ሲሆን ኣሁንም ፈተናው ዳግመኛ ላለመሰረቁ ምንም መተማመኛ ነገር የለም።
የትግራይ ትምህርት ቢሮ “የ12ኛ ክፍል ፈተና ፈታኞች የህወሓት ኣባሎች ኣስተማሪዎች ብቻ መሆን ኣለባቸው” የሚል ጭንቀት የወለደው መላ ኣውጥቶ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ያሉ ወረዳዎች ምልመላ ለማካሄ ጥረት ኣድርጎዋል። በተለይ በእንደርታና የሳምረ ሰሓርቲ ወረዳ ኣስተማሪዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።
በመቐለ ኣፄ ዮውሃንስ ፬ ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤትም ከደቡብ ምስራቅ የኣስተማሪዎች ተቃውሞ በመነሳት የህወሓት ኣባላት ያልሆኑና በኣይነ ቁራኛ የሚታዩ እምነት ያልተጣለባቸው የህወሓት ኣባላትም በደፈናው “ተቀንሳቹሃል” ተብለዋል።
* ድሮ በማትሪክ ፈተና የሚጨናነቀው ተፈታኝ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ብቻ ነበሩ። በኣሁኑ ሰዓት ግን ከተፈታኝ ይልቅ ፈታኙ መንግስ ኣጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ይገኛል።
መንግስት 12ኛ ፈተና ከስርቆት ለመታደግ መላ ጠፍቶት ተቸግሮ ይገኛል።


 

No comments:

Post a Comment

wanted officials