Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 11, 2016

የአማራ ተጋድሎ ከአቻምየለህ ታምሩ


የአማራው ትግል የመልካም አስተዳደር ትግል አይደለም። የአማራው ትግል የጭቆናና ለዲሞክራሲ የሚደረግ ትግል አይደለም። የአማራው ትግል የፖለቲካ ርዕዮተ አለም ትግል አይደለም። የአማራ ትግል ሀሳብ ተጥዶ «አማራ አለ? የለም» በሚል ጉንጭ የሚለፋበት ክርክር አይደለም።
13659053_293690970980031_9095508382608936044_n - Copy
ዛሬ አማራው ያጋጠመው መከራ ከፋሽስት ጥሊያን በላይ የከፋ የአማራ ስጋ የተራበ፤ የአማራ ደም የተጠማ የትግራይ ነጻ አውጭ የሚባል ጨካኝ አውሬ ነው። ፋሽስት ጥሊያን በጦር ወርሮ አገራችንን ከያዘ በኋላ የቅኝ አሳዳሪ መንግስት መስርቶ ነበር። ይህ ቅኝ አሳዳሪ መንግስት ድልድይ ሰርቷል፤ ዛፍ ተክሏል፣ መንገድ ዘርግቷል፤ ፋብሪካ አቁሟል፤ የጤና ተቋም ገንብቷል።
ዛሬ አማራው ያጋጠመው ጠላት የትግራይ ነጻ አውጭ ግን አማራውን ወርሮ የቅኝ አሳዳሪ መንግስት የሚመሰርት ብቻ ሳይሆን አማራውን ከምድረ ገጽ ጨርሶ በማጥፋት በአማራው መቃብር ላይ የትግራይን ሪፑብሊክ መንግስት የሚመሰርት የጠላት ጠላት ነው።
ዛሬ አማራውን ያጋጠመው ጠላት በጎጃምና ጎንደር፤ ወሎና ሸዋ የነበሩትን የድንጋይ ፋብሪካዎች፣ የወባ ማጥፊያ ድርጅቶት፣ የሲሚንቶ ፋብርካዎች፣ ወዘተ በመንቀል ወደ ትግራይ ነቅሎ የሚያጉዝ ዘራፊ ቡድን ነው።
ዛሬ አማራውን ያጋጠመው ጠላት በጎጃምና ጎንደር፤ ወሎና ሸዋ የበቀሉትን እድሜ ጠገብ ዛፎች እንደዘረፋቸው ፋብሪካዎቻችን ነቅሎ መውሰድ ስለማይችል ትግራይ ክልል ውስጥ ዛፍ እየተከለ አማራ ክልል ውስጥ ግን የትግራይ ባለሀብቶችን የእንጨት መሰንጠቂያ ፋብሪካ በማስከፈት የአማራውን የሚያራቁት ናዚ ነው።
ዛሬ አማራውን ያጋጠመው ጠላት አማራው እንዳይራባና መክኖ እንዲጠፋ የማምከኛ መርፌና ኤች.አይ.ቪ. ኤድስ የሚወጋ ኢሰብዓዊ ፍጡር ነው።
ዛሬ አማራውን ያጋጠመው ጠላት በአገሩ ብቻ ሳይሆን በቤቱም ጭምር እንዳይኖር ያደረገ አሳዶ ገዳይ፤ ደም መጣጭ፤ ረፍራፊ ዞምቢ ነው።

ስለዚህ አማራው ዛሬ የሚያደርገው ትግል የህልውና ትግል ነው። በመሆኑም የአማራው የዛሬ ትግል ከፋሽት ጥሊያን በላይ የከፋውን ጨካኝ የትግሬ ነጻ አውጭ ናዚ ለመደምሰስ የሚያካሂደው የሞት ሽረት ተጋድሎ ነው። ይሄ የሞት ሽረት ተጋድሎ የአርበኝነት ትግል ነው።
ዛሬ አማራ ባለበት ምድር ሁሉ ሞትና ግፍ ሽልማት ሆኗል። ጎንደር በሞት ሽረት እያቃሰተች ነው። ዛሬ የትግራይ ወሮ በሎች ጎንደርን አማራውን የሚያርዱበት የጦር አውድማ አድርገዋታል። አማሮች ወንድሞቼ! እህቶቼ! አማራውን በናዚ የትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን ላይ ይነሳ ዘንድ የምንችለውን ሁሉ ከማድረግ አንስነፍ። በተለይ በውጭ የምንኖርና ነጻነቱ ያለን አማራው በአንድነት ይነሳ ዘንድ እንጻፍ፣ እንግጠም፣ እንቀኝ፣ እንሸልል፣ እንተውን፣ እናጥና! ከሁሉም በላይ ግን በዚህ ሰዓት ሁላችንም እንከባበር፣ እንመካከር፣ እንደማመጥ፣ እንተማመን።


No comments:

Post a Comment

wanted officials