Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, July 15, 2016

በመዲናዋ የተበከለ የወንዝ ውሃ ጥቅም ላይ እየዋለ በመሆኑ የአተት በሽታ ስርጭት እየጨመረ ነው

በመዲናዋ የተበከለ የወንዝ ውሃ ጥቅም ላይ እየዋለ በመሆኑ የአተት በሽታ ስርጭት እየጨመረ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 23 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አንዳንድ ነዋሪዎች የተበከለ የወንዝ ውሃን ለተለያዩ ተግባራት መጠቀም ባለማቆማቸው የአተት በሽታ ስርጭት ከመቀነስ ይልቅ እየጨመረ መምጣቱን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ ይህን የገለጸው ለመንግስት ተቋማት ሃላፊዎች ስለ በሽታው ግንዛቤ ለማስጨበጥ ባዘጋጀው ውይይት ላይ ነው።
በከተማዋ በወንዞች ዳርቻ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች መፀዳጃ ቤቶቻቸው ከወንዝ ጋር በመያያዛቸውና ፍሳሹን በመልቀቃቸው ለአተት በሽታ ተዋህስያን መጋለጣቸውን በላቦራቶሪ ምርመራ መረጋገጡ ይታወሳል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመድ ኢማኖ እንደገለጹት፤ አንዳንድ ሰዎች የወንዞችን ውሃ ለህገ-ወጥ እርድ፣ ለአትክልት ማጠጫና ለዕቃ ማጠቢያ እየተጠቀሙበት በመሆኑ ችግሩ ከመቀነስ ይልቅ እየተባባሰ ነው።
በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ መረጃዎች በአግባቡ ጥቅም ላይ እየዋሉ አይደለም ያሉት አቶ አህመድ፥ ነዋሪውም በሽታውን ለመከላከል ሙሉ ለሙሉ ወደ ተግባር አልገባም ነው ያሉት።
በበሽታው የተያዙ አንዳንድ ሰዎችም በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት እየሄዱ አለመሆኑን ጠቅሰው፥ በሽታው በከተማይቱ ሁሉም ወረዳዎች እየተስፋፋ መምጣቱንም ተናግረዋል።
በሽታውን በአፋጣኝ መቆጣጠር እንዲቻልም በማናቸውም ምክንያት የወንዝ ውሃ ከመጠቀም መቆጠብ እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት።
ህብረተሰቡ የግልና የአካባቢውን ንፅህና በተገቢው ሁኔታ መጠበቅ ካልቻለ በሽታው የከፋ ጉዳት እንደሚያስከትል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials