በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ 44 የመድረክ አባላት አርሶአደሮች ታሰሩ
ሐምሌ ፬( አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ አርሶአደሮቹ የታሰሩት ማዳበሪያ አንወስድም ብለዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸው ነው ። ከታሰሩ 10ኛ ቀናቸውን የያዙት አርሶአደሮች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ከታሰሩትም መካከል የ80 ዓመት አዛውንትም ይገኙበታል። የአካባቢው የመድረክ ተወካይ እንደገለጹት አርሶአደሮቹ ማዳበሪያውን ለመውሰድ ያልፈለጉበት ምክንያት “ ተመጣጣኝ ዝናብ የለም፣ አንድ ጊዜ ከከፈልን በኋላ በተደጋጋሚ ክፍያ እንጠየቃለን “ የሚል ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በማዳበሪያ እዳ ሲሰቃዩ መቆየታቸውን ገልጸዋል። አድኑን ብለው መድረክ ጽ/ቤት መሄዳቸውን የገለጹት ተወካዩ፣ ፖሊሶቹ ጽ/ቤቱ ድረስ ገብተው አርሶአደሮችን አፍነው ወስደዋቸዋል ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ፖሊስ አዛዥ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
No comments:
Post a Comment