Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, July 5, 2016

ዩኒቨርስቲው በወሲባዊ ትንኮሳና ባልተገባ ወሲባዊ ተግባር የወነጀላቸውን በደሞዝ ቀጣ

ዩኒቨርስቲው በወሲባዊ ትንኮሳና ባልተገባ ወሲባዊ ተግባር የወነጀላቸውን በደሞዝ ቀጣ
=============
ዶ/ር አየለ ፍቅሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላለፉት አስር ዓመታት የአማርኛ ቋንቋን ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡የመምህሩ ተማሪዎችም አየለ ትጉህ መምህር እንደነበሩ ይመሰክራሉ ነገር ግን አሁን ለአስተማሪው ባህሪ የማይመጥን ክስ ቀርቦባቸው ለቅጣት መዳረጋቸውን እጄ ከደረሰ ደብዳቤ ለመረዳት ችያለሁ፡፡
መምህሩ ህብረት አብርሃም በተባለች የኦራል ሊትሬቸር ተማሪ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳና ተገቢ ያሆነ ወሲባዊ ተግባር በመፈጸማቸው የሶስት ወር ደሞዛቸውን እንዲቀጡ የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ማጽደቃቸው ተወስቷል፡፡
መምህሩ የተባለውን ድርጊት ፈጽመዋል አልፈጸሙም የሚለውን ክርክር ለግዜው ገታ አድርገነው ዩኒቨርስቲው በተማሪዎቹ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳና ወሲባዊ ተግባር(ይህ ምንማለት እንደሆነ ቢያሻማም)የፈጸመን መምህር በደሞዝ ቅጣት ብቻ ማለፉን እንዴት ይመለከቱታል? በተለይ በሴቶች ዙሪያ እንሰራለን የሚሉ ለዚህ ምን አይነት ምላሽ ይኖራቸው ይሆን?

No comments:

Post a Comment

wanted officials