Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, July 18, 2016

አራት የመንግስት ጋዜጠኞች ከወያኔ ሰርዓት ሽተው ተሰደዱ – በጋዜጠኛ ዘሪሁን አባተ

ከሬዲዮ ፋና እና በተለያዪ ቦታዎች በፍሪለሰን  የሚሰራው ጋዜጠኛ ቶማስ ሰብስቤ ፣ከኢ·ዚ ·አ ሊባኖስ ዪሃንስ ፣ ከአዲስ አበባ ቴሌቪዥን አመሃ ደስታ እና የቀድሞው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ሳምሶን ከተማ ናቸው ስርዓቱን የከዱት።
ጋዜጠኞች ባለፉት አመታት የተለያዩ በደሎች እንደ ደረሰባቸው እና በእየ ሚሰሩበት ጣቢያዎች ከእውነት የራቁ ዜናዎች ብቻ እንዲሰሩ እንደሚገደዱ ለቅርብ ጓደኞቻቸው ተናግረዋል።
በፖለቲካ እና ማህበራዊ ጉዳዪች ላይ የሚሰሩ ባልደረቦቻቸውም ይህን እውነታ ነግረውናል።
የገዠው ፓርቲ አባል እንዲሆን ጫና ይደረግባቸው እንደሆነም ደምተናል።በተለይ በልማታው ጋዜጠኝነት ሰም የህዝቡ ትክክለኛ ጥያቄ እንዳይሰራ ተደርገናል ።የመገናኛ ብዙሃኖቹ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ለገዢው ፓርቲ የሚጨነቁ ናቸው ብለዋል።
አንዳንዶቹም ለተቃዋሚ እና ለግል ሚዲያዎች መረጃ አሳልፋቹ ትሰጣላቹ እየተባሉ እንደሚገመገሙ እና ጫና እንደ ደረሰባቸው ለሳተናው  ሪፖርተር ነግረውታል።
በዘራቸውም  ሳቢያ የተገለሉ እና ከስራ የታገዱ እንዳሉ አጫውተውኛል።
ጋዜጠኞች ከሀገር እንዳይወጡ ብዙ ጥረት ተደርጎ ነበር።በእነዚህ መገናኛ ብዙሃንም ብዙ ጋዜጠኞች ሰራቸውን ለመልቀቅ አቃርበዋል።በጋዜጠኛ ዘሪሁን አባተ

Image result for fana radio news

No comments:

Post a Comment

wanted officials